ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገው እገዛ እያሳደገች ነው
ፎቶ፡ ኤይድ ቱ ቸርች ኢን ኒድ፡ ኤርትራውያን ስደተኞች በሰሜን ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በመስከረም 2016 በኒውዮርክ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ የገባችበት ባለ 9 ነጥብ ቃል ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ለስደተኞች ፍላጎት አጠቃላይ መርህ መጀመርዋን በይፋ ገለጠች፡፡
በእነዚሁ ቃል በገባችባቸው ነጥቦች መሠረት ኢትዮጵያ በአገርዋ የሚገኙት ስደተኞች እራሳቸው እንዲች ለማገዝ፣ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅተውላ በሰላም እየኖሩ በልማታዊ ስራዎች እንዲሳተፉ በማገዝ ጥረት የምታደርግ መሆንዋን በይፋ በስድተኞች አህጉራዊ ድርጅት የመረጃ መረብ ሪሊፍ ዌብ ተጠቅሷል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅሕፈት ቤት፣ አቶ ሰለሞን ተስፋየ የኢትዮጵያ መንግስት በስድተኞች ላይ ይከተለው የነበረ የቆየ አያያዝ በመቀየር፤ ለስደተኞች የሚሆኑ መጠለያዎች መገንባት፤ ከመጠለያዎች ተገላግለው ወይም ወጥተው ከአስጠጓቸው ህዝብና ሃገር ተዋድደው ኑሮኣቸው እንዲመሩ የሚያስችል አማራጮች እየፈለገች መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አቶ ተስፋየ ንግግራቸውን በመቀጠል “የኢትዮጵያ መንግሥት በሯን ለስደተኞች ክፍት በማድረግ ስደተኞችን በመጠለያዎች ታጥረው እንዲኖሩ አድርጎ የነበረው ፖሊሲ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ላለመቀጠል በዓይነ ኅሊናው ያስባል፤ ስደተኞችም ከመጠለያ ወጥተው ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሚቃናጁበት መንገድ እየተሰራላቸው ነው” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የኒውዮርክ በመስከረም 2016 የወጣው አዋጅ ስትቀበል፣ የስደተኞች ኑሮና ደኅንነት ለማሻሻል ማለት የሥራ ፈቃድና ሌሎች ጠቃሚ ዶኩሜንቶች እንዲያገኙ በማድረግ ረገድና ባሏት የኢንዳስትሪ ፓርኮችምም ሥራ የማስገኘት ዕድል ከፍ እንድታደርግ የመሳሰሉት እርምጃዎች እንድትወስድ ነው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን፣ (UNHCR) ዳይረክተርና አጠቃላይ የስደተኞች ፍላጎት መርህና የስራ ኃይል ቡድን አስተባባሪ፣ አቶ ዳንኤል እንድረስ እንደገለፀውም አዲሱ መርህ የስደተኞችን ህይወት በሚታይ መልኩ እያሻሻለ መሆኑን ተገለጠ፡፡ ከተገኙ ጥቅሞች ህፃናት ስደተኞች የትምህርት እድል የሚያገኙበትና ለስደተኞች የልደት ሰርቲፊኬት የሚያገኙበት ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው አስገንዝቧል፡፡
አቶ ዳንኤል ንግግራቸውን በመቀጠል፣ “ኢትዮጵያ ስደተኞችን በሚመለከት ልታከናውናቸው ቃል ከገባችባቸውና ዛሬ የምትሠራቸው ያሉት ሥራዎች ለብዙ የአፍሪቃ አገሮች በተምሳሌት ያነሳሳ ነው ” ብለዋል፡፡
ምንጮች፡
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መሠረት በአሁኑ ጊዜ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራና ከሱዳን የሄዱት ስደተኞች በኢትዮጵያ ከ850,000 በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ይገልፃል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ