ባህር ላይ የጠፉ ስደተኞች ለመለየት የሜድትራንያን ሀገሮች እቅድ አውጥተዋል፡፡

እንደ አለም አቀፍ ኮሚሽን ለጠፉ ሰዎች /አይሲኤምፒ/ ሚያዝያ 18 ዘገባ መሰረት 4 የአውሮፓ ሜድትራንያን ሀገራት ወደ አውሮፓ በባህር አደገኛ ጉዞ በሚያደርጉበት ጊዜ የሞቱ ወይም የጠፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ለመለየት እቅድ አውጥተዋል፤

ጣሊያን፣ ግሪክ፣ ማልታ እና ሳይፕረስ (ወደ አውሮፓ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ፣ እና እስያ ለበርካታ ስደተኞች መግቢያ የሆኑት አገሮች) በሰኔ 11 ሮም ላይ በሺ የሚቆጠሩ የጠፉ ስደተኞችን ጉዳዮችን ይፈታል የተባለውን እቅድ ለመወያየት ይሰበሰባሉ ፡፡ ጣሊያን ብቻ 8,000 የሚደርሱ ሬሳዎችን ሜድትራንያንን ውሃ ላይ ባለፉት 10 አመታት ሰብስባች. ሊቢያ እና ግብፅ እንደ ታዛቢነት ወደ ውይይቱ እንዲጋበዙ ይደረጋል፡፡
በቀጣይ 2 አመታት አይሲኤምፒ ሜድትራንያንን ሲያቋርጡ የሞቱ ሰዎችን ለመለየት እና ለመጠቆም የሚረዳ ፕሮግራም የሚነድፍ ይሆናል፡፡

ፕሮግራሙ በመጀመሪያ ያልተለዩ አካላትን ብዛት እና የተቀሩ ሬሶች የት እንዳሉ ወይም እንደተቀበሩ የሚገልጵ ሁኔታን ይገመግማል፡፡

በቂ የገንዘብ ምንጭ እስካለ 2ኛው ምዕራፍ ከ2019 በኋላ የሚጀምር ሲሆን ድርጅቱ የዲኤንኤ ናሙናዎች በመውሰድ የጠፉ ቤተሰብ አባላት ሪፖርት ካደረጉ ጋር ያነፃፅራል፡፡

አይሲኤምፒ ከበፊቱ የዩጎዝላቪያ ግጭት ምክንያት አይይዞ የተፈጠረ ሲሆን በባልከን ግጭት ከጠፉ 40ሺ ሰዎች መካከል 70% የሚሆነውን በስኬት ለይቷል፡፡ በ1995 በሰርቨኒካ የህዝብ ጭፍጨፋ ከተገደሉት 8,000 ሰዎች 90% የሚሆኑትንም የተወሳሰበ የዲኤንኤ ምርምር ዘዴ በመጠቀም መለየት የቻለ ተቋም ነው፡፡

ይህ የተራቀቀ የዲኤንኤ ቴክኖሎጂ ከራቁ ቤተሰቦች ናሙና በመውሰድ በሰነድ ያልተያዙ ስደተኞችን ለመለየት ያስችላል፡፡

እንደ አይሲኤምፒ ዋና ሓላፊ ካትሪኒ ቦምበርገር አገላለፅ “በአሁኑ ወቅት ይህን አጋጣሚ ለጠፉ ስደተኞችና አውሮፓ ውስጥ ለጠፉት 10ሺ ልጆች ለመለየት የሚረዳ ደረጃ ሊሆን የሚችል ክሰተት ላይ እየደረስን ነው” በማለት በጥቅምት ወር አይሲኤምፒ ዋና ጽ/ቤቱ ከሰርጄቮ ወደ ሄክ በሚያዞርበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

እንደ አይኦኤም (የተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ኤጀንሲ) መረጃ ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ 18ሺ ያህል ስደተኞች ወደ አውሮፓ በባህር መድረስ ችለዋል፡፡ ከ2010 ጀምሮ ቢያንስ 559 ስደተኞች ሜድትራንያንን ላይ መሞታቸው ወይም መጥፋታቸው ተዘግቧል፡፡

TMP – 19/05/208