በጋው በሚቃረብበት ወቅት ስደተኞች በፓሪስ ማደርያ ቸግሯቸዋል

ዮቶ ምንጭ: MSF

ሜዲስንስ ዱ ሞንዴ (MDM) እና ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) የተባሉ ሁለት ሰብአዊ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች፤ 1,000 የሚሆኑ ስደተኞች በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ በተለይም በከተማው ሰሜን-ምስራቅ ክፍል እና ሴን-ሳን-ሴኒስ በሚባለው አካባቢ ተበታትነው በመይመች ሁኔታ እንደሚተኙ ገልፀዋል፡፡
አብዛኞቹ ስደተኞች ምንም ዓይነት የሌሊት ልብስ እና ድንኳን የላቸውም፡፡

“ዝናቡ እና ፖሊሶች እዚህ ያለውን ሁኔታ መሸከም ከሚቻለው በላይ አድርገውታል፡፡ ዝናቡ በድልድዮች ስር ተሰባስበን እንድንጠለል ያስገድደናል፤ መጠለያ ካበጀን በኋላ ደግሞ ፖሊስ ይመጣና ከቦታው ዞር እንድንል ይነግረናል” ሲል አንድ ሱዳናዊ ስደተኛ ለድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ተናግሯል፡፡
“እኩለ ሌት ላይ ፖሊስ ይመጣና ከቦታው ያባርረናል፡፡ ሁሌም ‘ወዴት ዞር እንበል? የትስ መሄድ እንችላለን?’ ብለን በምንጠይቅበት ግዜ ‘እንጃ፤ ግን ከዚህ ዞር በሉ’ ይሉናል” ሲል ይጨምራል፡፡

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን የስደተኞቹ የጤና ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱን መታዘቡን እና በበጋው ወቅት ደግሞ ሊባባስ እንደሚችል ተናግሯል፡፡
“የአየር ሁኔታው እየቀዘቀዘ ነው፤ ስደተኞች ደግሞ ምንም ዓይነት የመኖርያ ቤት መፍትሄ ሳይደረግላቸው አሁንም ጎዳና ላይ እኖሩ ነው፡፡” ሲሉ የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን የፓሪስ ልዑክ ኃላፊ የሆኑት ኮሪኔ ቶሬ ተናግረዋል፡፡
“በሚገጥሟቸው አስከፉ ሁኔታዎች የተነሳ፤ ለቆዳ በሽታዎችና ለእከክ የመጋለጣጥ አደጋ ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ስጋት አለ፡፡”

ከኢትዮጵያ የመጣውና ፓሪስ ላይ ለአንድ ወር የቆየው ጀማል የሚባል ስደተኛ፤ የጎዳና ላይ ሂወት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙት የስደተኞች መጠለያ ካምፖችም እንደሚብስ ያምናል፡፡
“[አፍሪካ ውስጥ] የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት የስተደተኛ ካምፖች ያልተደራጁ እና እጥረት የበዛባቸው ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ቢያንስ መጠለያ ድንኳን፣ የሚበላ ነገር እና መረጃ ማግኘት እንችል ነበር፤ ደህንነታችንም የተጠበቀ ነበር፡፡ እዚህ የምናገኘው ብቸኛው መረጃ አሉባልታ ነው ፖሊስ ደግሞ ልክ ወንጀለኞች እንደሆንን ሁሉ እርምጃ ይወስዱብናል፡፡”