ከሊቢያ በራስ ፍቃድ የመመለስ ጭማሪ በማሳየቱ ሳቢያ የማቆያ ተቋማት መዘጋት ጀመሩ

የስደተኞ አለም አቀፍ ድርጅት/ አይኦኤም/ ሪፖርት እንዳደረገው 23,302 ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ትውልድ አገራቸው ድርጅቱ ባለው የበጎ ፍቃድ በጎ አድራጎት ተመላሾች/ ቪኤችአር/ ፕሮግራም መሰረት ከጥር 2017 ጀምሮ ተመልሰዋል፡፡ ከህዳር ጀምሮ አይኦኤም 10,171 ስደተኞችን ከአውሮፓ ህብረት፣ አፍሪካ ህብረት እና የሊቢያ መንግስት እገዛ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አግዟል፤ ሌሎች 5,200 ስደተኞች ከአፍሪካ ህብረት አባላት በተገኘ ድጋፍ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

አይኦኤም በቅርቡ የመመለሻ ፕሮግራሙን ከፍ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የስደተኞች ጥቃት፣ ስቃይ፣ በጣም የተጨናነቁ ሁኔታዎች የሊቢያ ማቆያ ተቋም ውስጥ እንዳለ በወጣው አስደንጋጭ ሪፖርት ምክንያት የመመለስ ፕሮግራሙን ከፍ አደርጓል፡፡ በውጤቱም ሊቢያ ውስጥ ያሉ ስደተኞች ብዛት ከግንቦት 2017 ጀምሮ እንደ ሊቢያ የበላይ የመንግስት ሀላፊ በ80 በመቶ ቀንሷል፡፡

ብርጋዴር ጄኔራል መሀመድ ባሽር የክፍሉ ሀላፊ ሊቢያ ውስጥ መደበኛ ያልሆኑ ስደትን ለመፍታት የቁጥሩ የስደተኞች መቀነስ ከአገሪቱ 53 የስደተኞች ማቆያ ወደ 20ዎች እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ በመንግስት የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ሃሳባዊ ስራዎች ያላቸው ሁኔታም አመቺ እንዳለመሆኑ በጣም ለተጋለጡ ለተጎዱ በተለይ ሴቶች እና ልጆች ዝቅተኛ አገልግሎት ለመስጠት ይሞክራሉ፡፡

በዚህ አመት መጋቢት የአይኦኤም ሊቢያ የተልእኮ ሀላፊ ኦትማን ቤልቢሲ እንደገለፁት በሊቢያ ስደተኛ ማቆያ ማእከላት ስደተኞችን ማገዝ የቀጠልን ሲሆን ከዛ ውጪ ስደተኞችን ለማግኘት ጥረታችንን ጨምረናል፡፡

እንደ ቤልቢሲ የአይኦኤም የበጎ ፍቃድ ተመላሾች ኦፕሬሽን ከተስፋፋበት ጊዜ ጀምሮ ይፋ በሆኑ ማቆያ ማእከላት ያሉ ስደተኞች ብዛት በግምት በጥቅምት 2009 ከነበረው 20,000 ህዝብ ወደ 4,000 ህዝብ ቀንሷል፡፡

በ28/11/2017 አቡጃ ውስት በተደረገው የአፍሪካ ህብረት ኤዩ -አውሮፓ ህብረት ኢዩ ስብሰባ የኤዩ-ኢዩ-ዩኤን የድርጊት ሀይል ታስክ ፎርስ ተቋቁሞ አላማው በስደት መስመር ላይ በተለይ በሊቢያ ውስት የሚሰደዱ ስደተኞች ስቃይ ለማስቀረት እና በተጨማሪም ወደ ትውልድ ሀገራቸው በበጎ ፍቃድ የሚመለሱትን ለማፋጠን ይሰራል፡፡

የፎቶ ክሬዲት ፡ኤምኤስኤፍ/ጉላውሚቢኔት /ማይኦፕ፡ አቡሳሊም ማቆያ ማእከል ትሪፖሊ፣ ሊቢያ የተያዙ ወንዶች

TMP – 17/05/2018