የተመድ ሪፖርት የሊቢያ የፀጥታ ሰራተኞች ከህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ሲል ከሷል
የፎቶ ምንጭ: ሬውተርስ/ሃኒ አማራ፡፡ ሊቢያ ጋርያን ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ስደተኞች ተቀምጠው ይታያል፤ በፈረንጆቹ ጥቅምት 12/ 2017፡፡
ሬውቶርስ እንደዘገበው፤ የተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች ቡድን ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው አብዛኞቹ ህገወጥ የሰው ዝውውር መረቦችና ታጣቂ አማፅያን ሊቢያ ውስጥ ከሚገኙ መንግስታዊ የፀጥታ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው፡፡
”የሌላ ትልቅ ፖለቲካዊና-ወታደራዊ ጥምረት አካል የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች፤ ህገወጥ በሆኑ የዝውውር ተግባራት ላይ የተሰማሩ ናቸው፤ በተለይም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ” ሲሉ ባለሞያዎች 15-አባላት ላሉት የፀጥታ ምክርቤት ኮሚቴ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ እነሱ እንደሉት ታጣቂ ቡድኖቹ “መንግስታዊ የፀጥታ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው”
ይህ የባለሙያዎች ኮሚቴ “ታጣቂ ቡድኖች እና ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች የመንግስትን ተቋማት እና ሃብት የስደተኞች መተላለፍያ መንገዶችን ለመቆጣጠር ያስችላቸው ዘንድ እየተጠቀሙባቸው ሊሆን እንደሚችል” ያላቸውን ስጋት አንስተዋል፡፡
ሪፖርቱ በፈረንጆቹ 2016 ላይ ትሪፖሊ ውስጥ በልዩ የመከላከያ ሃይል (SDF) ታስረው የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞችን የጠቀሰ ሲሆን፤ ይህ ዓለምአቀፍ እውቅና ካገኘው መንግስት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው ታጣቂ ሃይል ኤርትራውያን ስደተኞቹን አሳልፎ ለተለያዩ ህገወጥ የሰው ዝውውር መረቦች እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
“ይህ አጥኚ ቡድን የ SDF አመራሮች ይህ ከስራቸው የተከናወነውን የሰዎች ዝውውርና ግንኙነት በተመለከተ የሚያቅ እንደሆን እየመረመረ ነው” ሲል አጥኚው ቡድን ፅፏል፡፡
የ SDF ቃልአቀባይ አህመድ ቢን ሰሊም ለሬውቶርስ በሰጡት የፅሁፍ መግለጫ ላይ ሃይሉ “ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም” በማለት ክሱን ያጣጣሉ ሲሆን፤ SDF “ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን እየተዋጋ ነው ብዙ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችንም አስሯል” ሲሉ አክለዋል፡፡
ሪፖርቱ በተጨማሪም ህገወጥ ስደትን የሚዋጋው የሊቢያ ተቋም የእስር ማዕከላቱን አይቆጣጠርም ሲል ጠቅሷል፡፡ ይህም ስደተኞች ታስረውባቸው የነበሩ ማዕከላት በታጠቁ አካባቢያዊ ሃይሎች ስር የነበሩ መሆናቸውን በመጥቀስ አረጋግጠዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድጋፍ የሚደረግለት ብሔራዊ ጥምር መንግስት (GNA) “የስደተኞችን ፍሰት በመቆጣጠር ረገድ ታጣቂ ሃያሎች ከመንግስት ባለስልጣናት ይልቅ ጠንካራ መሆናቸውን“ ለአጥኚ ቡድኑ አምኗል፡፡
ይህ 157-ገፆችን የያዘውና ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት የተላከው ሚስጥራዊ ዘገባ በተጨማሪ አንደሚለው፤ አይኤስ አይኤስ ምንም እንኳ በፈረንጆቹ 2016 ሲርጥ ላይ ሽንፈት ቢገጥመውም አሁንም ቢሆን በማዕከላዊና ደቡባዊ ሊቢያ ህዋሳቱ መንቀሳቀሳቸውን ቀጥሏል ደቡብ ሊቢያ ላይ ከሚገኙ ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ጋር መቀላቀል እንደሚፈልጉም ጠቁሟል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ