የፀረ-ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሕጎች ስደተኞችን የሚረዱ ሰራተኞችን ለመክሰስ እየተጠቀሙበት ነው

ፎቶ ክሬዲት ጌቲ ኢሜጅድ / ካርል ኮርት

ቨኣይ. አር.አር /የሰው ዘር ግንኙነት የሚያጠና ኢንስቲትዩት ባካሄደው የስድስት ወራት የማጣራት ስራ እንደሚያስረዳው የእርዳታ ሰራተኞችን ኢላማ ያደረገና ሆን ተብሎ በመላው የአውሪፓ ሃገሮች የፀረ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሕጎች እየተሰራበት መሆኑና የሰብአዊ እርዳታ እንቅስቃሴ ለማዳናቀፍ እየተጠቀሙበት መሆኑ ታውቋል፡፡

ኢንስቲዩቱ እንደሰነደው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 45 የሰብኣዊ እርዳታ ሰራተኞችን በፀረ-ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሕግ እንደተከሰሱ ታውቋል፡፡

ከነዚህ በምሳሌነት የምትጠቀስ የ43 ዓመት ሴትና ነዋሪነቷ በሰዊዘርላን የሆነችና እንደ ዘጋርድያን ዘገባ በስደተኞች ዘንድ ማዘር ቴሬዛ የሚል ቅፅል እንደተሰጣትና ይህም በሰብአዊ እርዳታ ስራዋና በጣልያን ባህር ጠረፍ ለታገቱት የምግብ አቅርቦት በማድረጓ መሆኑ ታውቋል፡በዚህ ዓመት መስከረም ወር ሴትየዋ ለስደተኞችና ወላጅ የሌላቸው ህፃናት በማገዝዋ እስር እንደተፈረደባትና ሌላም ቅጣት እንደተጣለባት፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በፈረንሳይ አገር በካሌይ የስደተኞች ካምፕ ስደተኞችን የሚረዱ የበጎ ፈቃደኞች /የምግባረ-ሰናይ/ ሰራተኞች በአካባቢው ባለስልጣናት ስቃይና እንግልት እንደሚደርስባቸው ታውቋል፡፡ በመጋቢት ወር የቻሪቲ ሮያ ሲቶይን ሰራተኞች የሆኑት ሰዎስት የፈረንሳይና የእንፍሊዝ በጎ ፍቃደኞች እንደታሰሩና ይህም ለስደተኞች ምግብ፣መጠልያና ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማቅረባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
የኢንስቲዩቱ ዘገባ እንደሚያስረዳው የበጎ ፈቃድ ሰራተኞች የእርዳታ ሰራተኞችን ኢላማ ያደረገ ቅጣት መሆኑ ታውቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የድንበር ጠባቂ ሃይሎች /ፍሮንቴክስ/ በመባል የሚታወቁትን ቡዱኖች እንደከሰሳቸውና ስደተኞችን ወደ ሜዲተራንያን ባህር ዳርቻ በማጓጓዛቸው እንደተከሰሱ ዘገባው ያስረዳል፡ በዚህም ምክንያት ዘገባው የፍሮንቴክስ ሰራተኞችን አጥብቆ ይተቻል፡፡ ይህም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን፣ የእርዳታ ሰራተኞችንና የነፍስ አድን ሰራተኞችን ለማናናቅና ሕጋዊነታቸውን ለማነኳስስ መሆኑ ታውቋል፡፡

የአይ አር አር / የኢንስቲዩቱ/ ዘገባ እንደሚለው ለአውሮፓ ህበረት ደብዳቤ እንደሚፅፍና ይህም ለሰብአዊ እርዳታ ስራዎች እንደዲግፍና የእርዳታ ሰራተኞችን ከመወንጀል እንዲቆጠቡ ለማሳሳብ መሆኑ ታውቋል፡፡