የስደተኞች ፕሮጀክት ጣሊያን የአዳኞችን መርከብ ያዘች

የጣሊያን አቃቤ ህጎች ፕሮአክቲቫ ኦፕን አርምስ የተባለ የእስፖንሽ በጎ አድራጎት ድርጅት የሰዎች አዳኝ መርከብን እንዲያዝ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ መርከቡ የስደተኞችን አሰሳ እና የማዳን ኦፕሬሽን በሜድትራኒያን ባህር ላይ እያደረገ ነበር፡፡
በሲሲሊ የሚገኘው ፍ/ቤት መርከቡ በ 8/7/2010 ፖዛሎ በሚባለው የሲሲሊ ወደብ የደረሰበትን ምክንያት ለማጣራት ጊዜያዊ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን በወቅቱም መርከቡ 218 ያህል ስደተኞችን ይዞ ነበር፡፡
በ6/7/2010 ኦፕን አርምስ ስደተኞቹን የማዳን ተግባር ውስት ሳለ የሊብያ የወደብ ጠባቂዎች የማዳን ተግባሩ የእኛ ስልጣን ነው በማለት የተቃወሙ ሲሆን ስደተኞቹንም ካላስረከብዋቸው የጦር መሳሪያቸውን በማንሳት እንደሚተኩሱ ማስፈራራታቸው ታውቆዋል፡፡
የፕሮአክቲቫ ኦፕን አርም ዳይሬክተር ኦስካር ካምፓስ ለሬውተርስ እንደገለጹት የእነሱ ተቀዳሚ ተግባር ህይወትን ማዳን ነው፡፡ “በዛሬው ጊዜ ህይወትን ማዳን እንደወንጀል ተቆጥሯል” በማለትም አስገንዝበዋል፡፡
ይህ ጉዳይ በባህር ውስት በሰዎች ህይወት ላይ የሚደርስ አደጋን ለመታደግ በተነሳሱ የህይወት አዳኝ ድርጅቶች እና አደገኛ የሆነ ባህር ማቋረጥ የሚሞክሩ ሰዎችን ለማቆም በሚጥሩ የአውሮፓ ባለስልጣኖች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውጥረት መኖሩን ያመለክታል፡፡
የሲሲሊ ፍ/ቤት መርከቡ በቁጥጥር ስር እንዲውል ያዘዘው አባላቱ አለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝ ስምምነት ጥሰት ማደረጋቸውን በመጠርጠር እና ህገወጥ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ተባብረዋል በማለት ነበር፡፡
ሊብያውያኑ የሰው አዳኝ መርከቡ ይንቀሳቀስ የነበረበት ክልል በአለም አቀፍ ስምምነት መሰረት በሊብያ ቁጥጥር ስር በሚገኝ የባህር ክልል ውስት እንደነበረ ቢገልጹም የፕሮአክቲቫ ጠበቃ የሆኑት ሮዛ ኢማንዌላ ሎፋሮ ኦፕን አርምስ የዚህ አይነት አለም አቀፍ ስምምነት እንዳለ አያቅም ብለዋል፡፡
በካታኒያ ሲሲሊ ውስት የሚገኙ ጠበቃዎች በበኩላቸው መርከቡ ለእስፓኒሽ ባለሥልጣኖች ጣሊያን ለማረፍ ፍቃድ መጠየቅ እንዳለበት እያወቀ መረጃ ሳይሰጥ ብመቅረቱ እና ጉዞውን ወደ ሰሜን ጣሊያን መሬት ለመድረስ በመጣሩ ከሰዋል፡፡
ካፒቴኑ, የተሳፋሪዎች አስተባባሪ እና መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት ዳይሬክተር ህገ ወጥ የኢምግሬሽን አላማ ጋር በተያያዘ የወንጀል ክስ በምርመራ ላይ ይገኛሉ፡፡
ፕሮአክቲቫ ተግባራቱ በባህር አደጋ ላይ ያሉ ሰዎችን ህይወት ከማዳን ፍላጎት ብቻ የመነጨ መሆኑን ገልጶዋል