አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በ2017 በ10,000 ስደተኞችን ወደ አገራቸው ይመልሳል
TMP – 16/04/2017
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አብዛኞቹ አፍሪካውያን የሆኑና በሊቢያ የሚገኙ 10,000 ስደተኞችን በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ አገራቸው ለመመለስ አቅዷል፡፡
በ2016 ድርጅቱ አውሮፓውያን ድጋፍ 2,775 ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያደረገ ሲሆን በዚህ ዓመትም ከ7,000 እስከ 10,000 ስደተኞችን ለመመለስ አቅዷል፡፡
ድርጅቱ ሊቢያ ውስጥ ያለስራና ገንዘብ የሚገኙ በበጎፍቃደኝነት ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ዝግጁ የሆኑ ስደተኞችን ድጋፍ ያደርግላቸዋል፡፡
አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ የተቀናጀ የድጋፍ ፕሮግራም እንደሚያደርግም ተገልጧል።
ድርጅቱ እንደገለፀው ሊቢያ ውስጥ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ምክንያት ከ2016 መጨረሻ ወዲህ ከስደተኞች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ብዙ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እስከ አሁንም በዚህ ዓመት 1,755 ስደተኞች እንደመለሰና ሌሎች 5,000 ያለ ረዳት የሚገኙ ስደተኞችም ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ድጋፍ እንደሚሹ ገልጿል። አብዛኛዎቹ ያለመለያ ዶኩመንት የሚገኙ ስደተኞች በሊቢያ እስርቤቶች ለረጅም ጊዜ ታጉረው የቆዩ ናቸውና ብሏል።
ሊቢያ ውስጥ ቆይተው ወደ ሃገራቸው ከተመለሱት ስደተኞች ከናይጄሪያ፣ ሴኔጋልና ማሊ የመሳሰሉ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የመጡት በቁጥር እንደሚልቁ የተገለፀ ሲሆን ከምስራቅ አፍሪካና ባንግላዲሽም እንደሚገኙባቸው ድርጅቱ ገልጿል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ