ሃንጋሪ ሁለተኛው የስድተኞች የድንበር አጥር ግንባታ ኣጠናቀቀች
ሃንጋሪ ከሰርቢያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ሁለተኛው የድንበር አጥር ስድተኞች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡ የድንበር አጥሩ 155 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለውና በማስጠንቀቅያ ደወልና ካሜራ የተገጠመለት መሆኑ ታውቋል፡፡
አዲሱን የድንበር ላይ አጥርን የጎበኙት የአገር ውስጥ ሚኒስተር ዋና ፀሓፊ ካሮሊ ኮንትራት እንዳስገነዘቡት የሃንጋሪ የመከላከያ የድንበር ላይ አጥር ከመቸውም ግዜ የጠነከረ ነው፤ ሃንጋሪ ድንበርዋን በመከላከል የሸንገን ዞንን እየተከላከለች ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የሃንጋሪ መንግስት ሁለተኛው የድንበር ላይ አጥሩን ለመገንባት የወሰደው ከስደተኞች የሚመጣውን ጫና ለመቋቋምና ካለፈው ጫና የሚበልጥ እንደሚሆን ካሁኑ ለመዛጋጀት መሆኑ ገልፀዋል፡፡ የስድተኞች በብዛት መጉረፍ በዚህ 2 ዓመታት ለአውሮጳ ጉዳት መሆኑ እንደቀጠለ ነው፡፡ የባልካን ሃገሮች የጉዞ መስመር ሁሌ የሚጨናነቅና በተለይም ክረምት ሲገባ ቁጥራቸው የበዛ ስድተኞች ወደ አውሮጳ እንደሚያቀኑ ኮንትራት/ሓላፊው/ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ሃንጋሪ በቅርቡ የጥገኝነት ፍቃድ አሰጣጥ ፖሊስዋ ጠበቅ አድርጋለች፡፡ የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች መጠየቅ የሚችሉት በሁለት የድንበር ዞኖች ብቻ መሆኑና በቅርቡ በወጣው ህግ መሰረት ስደተኞች መታሰራቸውና በኮንቴይነር እንዲቆዩ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የሃንጋሪ የድንበር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ ወደ አገሯ የሚገቡ የስደተኞች ቁጥር ቀንሰላታል፡፡ ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሂህ ከዚህ ዓመት መጀመርያ ጀምሮ ወደ 165 ሰዎች ብቻ ናቸው ድንበር ተሻግረው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሃገሯ የገቡት፡፡
የሁለተኛው የድንበር አጥር ግንባታ የተጀመረው በዚህ መጋቢት ወር ነው፡፡ በ2015 ሃንጋሪ የገነባቻቸው የድንበር አጥሮችን በደቡብ ከሰርቢያና ክሮሽያ የሚያዋስኗት ናቸው፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ