በቱርክ የባህር ዳርቻ የስደተኞች ጀልባ ሰምጣ 11 ሰዎች ሞቱ

TMP – 21/04/2017
በቱርክ የባህር ዳርቻ ኩሳዳሲ ከተማ አቅርብያ 22 ህገወጥ ስደተኞችን የጫነች ከፕላስቲክ የተሰራች አነስተኛ ጀልባ በመስመጧ የሞቱ 11 ሰዎች ሬሳ መገኘቱና የ4 ሰዎች ግን አለመገኘቱን ተገልጿል፡፡

የቱርክ ዶጋን የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሞቱት ውስጥ አምስት ህጻናትና ሁለት ሴቶች ይገኙበታል፡፡ አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ ግሪክ ደሴት በህገወጥ መንገድ ለመግባት የተነሱ ሶርያውያን ናቸዉ፡፡ ሁለት ቱርካውያን ህገወጥ አዘዋዋሪዎችም በህይወት ከተገኙት መካከል በቱርክ የባህር ጠባቂዎች መያዛቸዉ ተገልጿል፡፡

አደጋዉ የተከሰተዉ 250 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ዳርቻ መሞታቸዉ ከተዘገበ ከአንድ ቀን በኃላ ሲሆን የስፔን የእርዳታ ድርጅትም ከ100 እስከ 120 እንደጫነችና 5 ሬሳዎች በቁጥጥር ስር በዋለችው አነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ተንሳፈዉ አግኝተዋል፡፡

በቱርክና አውሮፓ ህብረት መካከል የቱርክን ደሴቶች አቋርጠው ወደ አውሮፓ የሚያልፉ ስደተኘኞችን ለመግታት ስምምነት ከተፈጸመ በኃላ አብዛኛዎቹ በኤጅያን ባህር አደገኛ ጉዞ ማድረጋቸዉ ቀጥለዋል፡፡