ጸረ ስደተኘች ጥቃት በኦስትራ እየጨመረ ነው

TMP – 17/04/2017

የኦስትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዘገባ እንደሚያሳየው በስደተኞች መኖርያና በጥገኝነት ጠያቂዎች መጠልያ አከባቢዎች የሚደርሰው ጥቃት በ2016 ከ 2015 ሲወዳደር በእጥፍ መጨመሩ ያሳያል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ ባለፈው ዓመት ብቻ 49 ጥቃቶች ሲመዘገቡ በ2015 ከተዘገበው 25 ጥቃቶች በእጥፍ መጨመሩ ያሳያል፡፡ የተመዘገቡት ጥቃቶች ከዘረኛ የሆኑ የስእል ስራዎች እስከ ድንጋይ ውርወራ በመስኮትና የጋዝ ቧንቧ እስከመቁረጥ ይደርሳል፡፡

የግሪን ፓርቲ ፖለቲከኛ የሆኑት አልበርት ስቴይንሃውሰር ሲናገሩ 44 የሚሆኑ ጥቃቶች ከጥላቻ የመነጩ መሆናቸው ለኦስትራ ፕሬስ ኤጀንሲ ሲገልፁ ከነዚህም 77% የሚሆኑት ጉዳዮች ያልተፈቱ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

የእንቅስቃሴ መሪዎች ሌሎች ብዙ ጥቃቶች እንደደረሱና ከ49 የበለጡ ጥቃቶች እንደተዘገቡ ይገልፃሉ፡፡

ሪፖርቱ እንደጋለጠው ሌሎች 49 ጥቃቶች በስድተኞች ራሳቸው በመጠልያዎች እንደደረሱ፤ ይህም ከግጭት እስከ ግድያ ዛቻና ዝርፍያ እንደደረሰ፤ ስድተኞቹ በግጭት ቀስቃሽ መሆናቸው ለራሳቸው ምን አስተዋፅኦ እንዳለው ስቴይንሃውሰር ሲናገሩ “የኚህ ግጭት መነሻዎች ምን እንደሆኑ ማየት አለብን፡” ብለዋል። “በትልቁ የምንጠረጥረው የስነ አእምሮ ችግር፣ የጦርነት ተሞክሮና ከመጠን ያለፈ ግጭት ትልቅ ሚና አላቸው፡” ብለዋል።

አገሪቱ ለቀው ለመውጣት ፍቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞች ኦስትራ 130,000 የጥገኝነት ጠያቂዎች ለማስተናገድ እየታገለች መሆኗና ስደተኞችን በተመለከተ አዲስ ሕግ ማውጣቷና ይህም ሕግ ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመሄድ ፍቃደኛ ካልሆኑ ሀገሪቱን ለቀው የማይወጡ ከሆነ መጠልያ እንደማይሰጣቸውና ኦስትራ የባልካን አገሮች የመከላከያ ፕሮጀክት ውስጥ መግባቷ ይህም 15 የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች ያካተተና ከወደ ሰሜን የሚደረገው የስደተኞች ፍልሰት የሚገታ መሆኑ ታውቋል፡፡

ፀረ ስደተኞች ጥቃቶች ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች በቁጥር እየጨመሩ ነው፡፡ ጀርመን ከ900 ጥቃቶች በስደተኞች መኖርያ እንደደረሱ በ2016 ተመዝግበዋል፡፡ ተመሳሳይ ዘገባዎች ከታላቋ ብሪታንያም ከጥላቻ ጋር የተዛመዱ ወንጀሎችና ስድተኞችን አላማ ያደረጉ በ50%  በ2015 እና በ2016 መጨመራቸው  የተባበሩት የአውሮፓ ሕብረት ኤጀንሲ ለሰብአዊ መብቶች የ 2016 ዘገባ አውጥቷል፡፡ ዘገባውም ከ14 የአውሮፓ ሃገሮች የግጭት፣ የፆታዊ ትንኮሳና ዛቻ እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮች ስደተኞችን በተመለከተና ጥገኝነት ጠያቂዎችንና ልጀቻቸው ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይገለፃል፡፡