75 ኤርትራዉያን ስደተኞች በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ሞቱ

TMP – 10/03/2017

አሰና የተባለ የኤርትራ ነጻ የድረገጽ ሚድያ እንደዘገበዉ ከሆነ 75 ኤርትራዉያን ስደተኞች  የሞቱት በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በፌብርዋሪ 25 በህገወጥ አዘዋዋሪዎች መኪና ተሳፍረዉ ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኘዉ ድንበር ጥሰዉ ለማለፍ ሲሞክሩ ነዉ፡፡

የመጀመሪያዉ የመኪና ግጭት በተፈጠረበት ቅጽበት 51 ስደተኞች ወዲያዉ የሞቱ ሲሆን 27 በከባድ መቁሰላቸዉም ተዘግቧል፡፡ በከባድ ከቆሰሉት 27 ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደ ገዳሪፍ ሆስፒታል በሚጓዙበት ወቅት 25 ሆስፒታል ሳይደርሱ የሞቱ ሲሆን በአጠቃላይ ከ78 ስደተኞች ሁለቱ በከባድ ቆስለዉ ሆስፒታል ዉስጥ እንደሚገኙም ተዘግቧል፡፡

ስደተኞቹ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከነበሩበት የስደተኞች መጠለያ በህገወጥ ደላሎችና አዘዋዋሪዎች ወደ ሱዳን ያለምንም ችግር እናሻግራችኀለን ተብለዉ ነዉ የወጡት፡፡

“እንደዚህ ዓይነት ዘግናኝ አደጋ ከዚህ በፊት በህይወቴ አይቼ አላዉቅም” ያሉት የገዳሪፍ የጸጥታ ኃላፊ አልዳዉድ ሰይድ መሐመድ ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች አንዱ በገደሪፍ ባስስልጣናት አንዱ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ለአደጋዉ ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆኑ 7 ህገወጥ የሰዉ ንግድ አዘዋዋሪዎች እና አንድ ደላላ ከኢትዮጵያ የመጠለያ ካምፕ ወደ ሱዳን በማጓጓዝ ወንጀል እንደሚፈለግ ገልጸዋል፡፡

አንድ ደላላ በኢትዮጵያ የመጠልያ ካምፕ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዉያንን በመደለል ወደ ሱዳን ያለምንም ችግር እንደሚገቡና ከዛም ወደ ሊቢያና ግብጽ በመዉሰድ ለቀጣይ መደረሻቸዉ ዝግጁ እንደሚያደርጉዋቸዉ ቃል በመግባት ነዉ ስደተኞችን ያንቀሳቀሰዉ