የአውሮፓ ህብረትና የኔዘርላንድስ መንግስት በኢትዮጵያ ለስደተኞች ፕሮግራም እርዳታ የሚውል የ30 ሚልዮን ዩሮ ፈቀደ

TMP – 04/03/2017

የስድተኞች ከሀገር ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ መውጣት ለመቀነስና በሃገር ውስጥ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ስድተኞችና ለነሱ መጠልያ የሰጠችው ኢትዮጵያ መረጃ የሚውል የአውሮፓ ህብረትና የኔዘርላንድስ መንግስት የ30 ሚልዮን ዩሮ ሰጥቷል፡፡

የአገር ውስጥ ፕሮገራም በተለይ በኢትዮጵያና ሱማሌ ስደተኞች ላይ ልዩ ትኩረት ያደረገ ሲሆን እነሱን ያጠለሉ ሕብረተሰቦችም ጭምር ለማገዝ ነው፡፡ ፕሮግራሙ የማህበራዊ አገልግሎቶችና የአከባቢ የኑሮ ሁኔታ ዕድል ለመክፈት መሆኑም ታውቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የስድተኞችን  የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ስደተኞች የሚያስተናግዱ የአካባቢው ማሕበረሰብ የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ከአከባቢው ወደ አውሮፓ ሃገሮች የሚደረጉን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደት ለማስቀረት ያለመ መሆኑም የአውሮፓ ህብረት ተስፋ ያደርጋል፡፡

ፕሮግራሙ ይፋ የሆነው  በየካቲት 22 በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቡዱን ሓላፊና በኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የትብብርና የዕድገት ምክትል ሓላፊ ኣንድ ላይ በመሆን ነው፡፡ ፕሮግራሙ የሚደገፈው በአውሮፓ ህብረት የአስቸካይ እርዳታ ድርጅት ለአፍሪቃ በተባለው ፈንድ ነው፡፡

ተመሳሳይ ፕሮግራም በኬንያ  የተቋቋመ ሲሆን  በእቅዱ ተይዘዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣናት፣በአካባቢው ህዝብና ከክልልና ፌደራል መንግስታትና ከሌሎች ባለድርሻ ኣካላት ጋር በጋራና በጥብቅ ትስስር ይሰራል፡፡

ሌሎች ብዙ የአውሮፓ ህብረት አገሮች የእርዳታ ትብብር ድርጅቶች ተመሳሳይ ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ለመክፈት እየሰሩ ነው፡፡ ይህም የህዝቦችን  የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል የተለያዩ ዕድሎች መፍጠር ለሕገ ወጥ ስደትና ኣደገኛ ጉዞዎችና የሰዎእ ዝውውር መግታት የመጀመርያውና ቁልፍ መፍትሄ መሆኑ ታምኖቦታል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ስደተኞች በማስተናገድና በማስጠለል ሁለተኛዋ ትልቅ ሃገርና 800,000 ስደተኞችን ከጎረቤት ቸገሮች በማስጠለልና ማስተናገድ ትታወቃለች፡፡