ኦስትርያ ህገወጥ ስደተኞች የሚያገኙት መሰረታዊ አገልግሎት ልታቋርጠዉ ነው

TMP – 17/03/2017

የኦስትርያ ፓርላማ በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ ገብተዉ የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ ዉድቅ የተደረገባቸዉ ስደተኞች

ሃገሪቱን ለቀዉ ካልወጡ ማንኛዉም መሰረታዊ አገልግሎት እንዳያገኙ የሚያደርግ ህግ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

የሃገሪቱ የሃገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ወልፍጋንግ ሶቦትካ እንዳሉት “ሃገሪቱን ለቀዉ እንዲወጡ የተወሰነባቸዉና

ፍቃደኛ ያለሆኑ ስደተኞች መጠለያና ምግብ ጭምር የማያገኙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል” ብለዋል፡፡

በኦስትርያ ስደተኞች መሠረታዊ የኑሮ አገልግሎት ማለትም ህክምና፣ ምግብና 40 ዩሮ ወርሃዊ አበል የሚያገኙ ሲሆን

ሃገሪቱን ለቀዉ እንዲወጡ የተወሰነባቸዉ ስደተኞች ይህ ጥቅም እንደሚቋረጥባቸዉ የገለፁት ስቦትካ “የመጀመሪያዉ

ነገር በዚህች ሀገር ለመኖር የሚያስችል ህጋዊ መብት የሌላቸዉ ስደቸተኞች ከመንግስት አንዳች ነገር እንደሚያገኙ ነዉ”

ብለዋል፡፡

ህጉ ሀሰተኛ መረጃ በሚሰጡ ስደተኞች ላይም የቅጣት ግዴታን ያካተተ ሲሆን እንደሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ስለማንነታቸዉ

ሃሰተኛ መረጃ በሰጡ ስደተኞች የ3 ወር አስራትና 5 ሺህ ዩሮ ቅጣትን የሚደነግግ አንቀጽም ተካትቶበታል፡፡ ትክክለኛ

የጉዞ ሰነድ ሳይኖራቸዉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስደተኞች ወደ መጡበት ለመመለስ የሚያስችል በአዉሮፕላን ጣብያዎች

አቅራቢያ የማገቻ ጣብያ ማቋቋምንም ህጉ ያካትታል ተብሏል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የአህጉሩን ድንበሮች መቆጣጠር አልቻለም የሚል ስሞታ ያላት ኦስትርያ ስደተኞችን ለመቆጣጠር

በ15 የምስራቅ አዉሮፓ ሃገራት የተቋቋመዉ የባልካን የመከላከያ ግንባር ፕሮጀክት መቀላቀሏንም ተዘግቧል፡፡

“የአዉሮፓ አህጉር ድንበሮች በበቂ ሁኔታ በአዉሮፓ ህብረት ጥበቃ ይደረግላቸዋል የሚል እምነት የለንም፣ ለዚህም ነዉ

ኦስትርያ ከ15 የምስራቅ አዉሮፓ ሃገራት በመጣመር አዲስ የባልካን መከላከያ ግንባር ፕሮጀክት ጋር ለመተባበር

የወሰነዉ፡” ሲሉ የኦስትርያ የመከላከያ ሚኒስትር ከጀርመን ብሄራዊ ጋዜጣ ዲ ቨልት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ

ተናግረዋል፡፡

ባለፈዉ ወር ኦስትርያ ህገወጥ ስደተኞችን ለመከላከል ወደ ሌሎች የአዉሮፓ ሃገራት የድንበር ጠባቂ ሰራዊት ለመላክ

የሚያስችል ህግ ለማጽደቅ እየሰራች እንደሆነም ዶስኮዚል ገልፀዉ ነበር ፡፡