ሃንጋሪ ስደተኞችን ለማቆም ሁለተኛ የስደተኛ ፕሮጀክት አጥር እየገነባች ነው
TMP – 13/03/2017
ሃንጋሪ ከጎረቤት ሰርቢያ በነፃነት የሚፈሱ ሕገ-ወጥ ስድተኞችን ለመግታትና ለማቆም በሃገሪቱ ሁለተኛ የሆነውን አጥር መገንባት ጀምራለች፡፡ እንደ አሶሼትድ ፕረስ ገለፃ ከሆነ 10 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ የሙከራ አጥር በመገንባት ላይ መሆኗና ከዚህ በፊት የተገነባውን አጥር ለማጠናከር በ2015 ባለስልጣናት ኣጥሩ መገንባታቸውና ሌሎችም የስለላ መሳርያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ታውቋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስተር ቪክቶር ኦርባን ቃል አቀባይ እንደገለፁት መንግስታቸው የስደተኞች ፍልሰት ለሃገሪቱና ለአውሮፓ ህብረት ትልቅ ስጋት በመሆኑ ሁለተኛው አጥር መገንባት አስፈላጊ መሆኑና በሚቀጥት ጊዜያት ተጨማሪ ስድተኞች በድንበርዋ አከባቢ ሊደርሱ እንደሚችሉ ትገምታለች ብለዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፒተር ሲዣርቶ ከሮማንያው ኣቻቸው ከተገናኙ በሃላ እንደተናገሩት “ምንም እንኳን የአውሮፓ ሕብረት የቱርክ ስምምነት ቢኖር የምዕራብ ባልካን መንገድ ቢዘጋም በማነኛውም ጊዜ የስደተኞች ፍልሰት ጫና ይኖራል ብለን እንገምታለን፡፡ በተለይ በደቡባዊ ድንበራችን ለዚህም ነው የመከላከል አቅማችን ለማጠናከር የደቡባዊ ድንበራችን የምናጣናክረው ብለዋል፡፡” የሁለተኛ አጥር ስራ ወድያውኑ የአየር ሁኔታዎች ሲመቻቹ ይጀማራል፡፡
መንግስት ለአዲሱ አጥር ግንባታ ወደ 38 ቢልዮን ፎሪነትስ (130.7 ሚልዮን ዶላር) ወጪ እንደሚያደርግና የመጓጓዣ ኮንቴይነሮች በሰርቢያ አዋሳኝ ድንበር በመጓጓዝ ላይ መሆናቸው ታውቀዋል፡፡ስደተኞች የከለላ ጥያቄዎች በሃንጋሪ ባለስልጣናት እስኪታይና እሰኪመረመር ጊዜ እዛው እንዲቆዩ ይገደዳሉ፡፡ ስደተኞችን ለመግታት የሚያስችል መንግስት አዲስ ሕግ ኣውጥቷል፡፡ ሕጉም ባለስልጣናት በ 5 ማይልስ ርቀት ከሰርቢያ የሚገቡ ስደተኞች ለመመለስ የሚያስችል ሕግና በሺዎች የሚቆጠሩ የድንበር ጠባቂዎችም አሰማርቷል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ