በሜዲተራንያን ባህር የሚሞቱት የስደተኞች ቁጥር ከአንድ ሺ በላይ አሻቀበ
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የቅርብ ቀን ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሰሜን ኣፍሪቃ የሜዲተራንያን ባህርን በማቋረጥ ወደ አውሮጳ ለመሻገር በሚያደርጉት ሙከራ 2017 ከገባ እስከ አሁን ድረስ የሟቾች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ ዘግቧል፡፡ ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ እንደሚበልጥ ነው፡፡
ከነዚህ ሟቾች ከ150 በላይ የሚሆኑት ህፃናት ናቸው፡፡ እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ ከሆነ ትክክለኛ የህፃናት ሟቾች ቁጥር ከዛም በላይ እንደሚሆንና አብዛኛው ግዜ ህፃናት ያለ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ለብቻቸው እንደሚጓዙና በትክክልም ቁጥራቸው እንደማይታወቅ ነው ዘገባው የሚያመለክተው፡፡
የዩኒሴፍ የአከባቢው ዳይሬክተርና በአውሮጳ የስደተኞች ቀውስ ልዩ አስተባባሪ አፍሻን ካን እንደገለፁት የአደጋው ሰለባ የሆኑት ሰዎች በሺህ የሚቆጠሩ ህፃናትን ጨምሮ ወደ አውሮጳ ለመሻገር ይህንን አደገኛ የጉዞ መስመር መጠቆማቸው ህይወታቸውን ለአደጋ ማጋላጣቸው ያሳስባል ብለዋል፡፡
ባለፈው ሚያዝያ ወር ቢያንስ 97 ሰዎች ከነዚህ ውስጥ 15 ህፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ ስድተኞችን የጫነ የፕላስቲክ ጀልባ ሰጥሞ ከሊብያ ባህር ጠረፍ አቅራቢ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ታውቋል፡፡
በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የጠፉት ስደተኞች ፕሮጀክት እንደዘገበው ፡ ይህ ከሰሜን አፍሪቃ ወደ አውሮጳ የመሸጋገርያ የጉዞ መስመር አደገኛነት እንደቀጠለና ፤ በዓለም ላይ ካሉት አደገኛ የስደት ጉዞ መስመሮች አንዱ መሆኑን ነው።
ፅሑፉን ያካፍሉ