ሳብራታ ውስጥ በተቀሰቀሰው ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እየተጎዱ ነው

የፎቶ ምንጭ: ሬውቶርስ/ሃኒ አማራ፡፡ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ በምትገኘው የሳብራታ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የእስር ማዕከል ስደተኞች ምግብ ለመቀበል ሲጠባበቁ፤ ጥቅምት 9 /2017፡፡

ለሶስት ሳምንታት በዘለቀውና ከትሪፖሊ በስተምዕራብ 78 ኪሎሜትሮችን ርቃ በባህር ዳርቻ የምትገኘውን ሳብራታ የምትባለውን ከተማ ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ውጊያ ብዙዎች ሞተዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል እንዲሁም ደግሞ ብዙ የአካባቢው ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ በዚሁ መሓል፤ በታጠቁ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ታስረው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ግን መሄጃ አጥተው ታግተው ነው የሚገኙት፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) በፈረንጆቹ ጥቅምት 9 እንዳለው፤ በዚህች በባህር ዳርቻ አቅራቢያ በምትገኘው ከተማ ውስጥ ለሚገኙት ስደተኞች ሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በሊቢያ የ UNHCR ተወካይ የሆኑት ሮቤርቶ ሚኞን እንዲህ ብለዋል: “ሁኔታው አሁንም ያልተረጋጋ ነው እኛም ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተልነው ነው፡፡ ድጋፍ ለሚያሻቸው ዕርዳታ ለመስጠት በቦታው ላይ ከሚገኙ አጋሮቻችን ጋር እየሰራን ነው፡፡”

በሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ ከምትገኘውና ዋና የስደተኞች ህገወጥ ዝውውር መነሃርያ ከሆነችው የሳብራታ ከተማ በመነሳት ይደረግ የነበረው በርካታ የስደተኞች የባህር ላይ ጉዞ በሓምሌ ወር በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል፤ ይህም ሊሆን የቻለው አንድ የታጠቀ ቡድን በተባበሩት መንግስታት ከሚደገፈው የትሪፖሊ መንግስት ጋር ጉዞዎችን ለማገድ ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ነው፡፡
ስምምነቱ በኋላ ላይ መስከረም 17 ጀምሮ ጥቅምት 6 ላይ ያቆመው ውጊያ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል፤ ውጊያው የቆመው ፀረ-አይኤስ የዘመቻ ህብረት ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው፡፡
UNHCR እንዳለው፤ ውጊያው ከቆመ በኋላ የአካባቢው ባለስልጣናት ቢያንስ 6,000 ስደተኞች ታስረውባቸው የነበሩ በርካታ ይፋዊ ያልሆኑ የእስር ማዕከላትን ተቆጣጥረዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርጉዝ ሴቶች፣ ጨቅላ ህፃናት እና ጠባቂ የሌላቸው ህፃናት የሚገኙባቸው 4,000 የሚደርሱ ስደተኞች በከተማዋ ወደሚገኝ መጠለያ እንዲዘዋወሩ ተደርጋል ብሏል ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM)፡፡

“በቅርቡ ሳብራታ ውስጥ በተከሰቱ አዳዲስ ሁኔታዎች መሃል ታግተው የሚገኙ በርካታ ስደተኞች መኖራቸው በእጅጉ አሳስቦናል” ብለዋል የ IOM የሊቢያ ልዑክ ኃላፊ የሆኑት ኦትማን ቤለቤሲ በሰጡት መግለጫ፡፡

“ሊቢያ ውስጥ ለሚገኙት ስደተኞች ከእስር ሌላ አማራጭ ሊፈለግላቸው ይገባል”