ኢትዮጵያ የኤርትራ ዜጎችን መመዝገብ ከጀመረች ወዲህ የታየው ከፍተኛ መሻሻል
ፎቶ ያነሳው፡ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን/ዲያና ዲያዝ፡፡ የኦቾካኦ ልጅ አሪያት፣ በመጀመርያ ከሄዱት ሕፃናት ስደተኞች መካከል በኢትዮጵያ የልደት ምስክር ወረቀት የተቀበለ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በአገርዋ. የኤርትራ ዜጎችን የመመዝገብ ሂደት በህጋዊ መንገድ ክፍት አደረገች :: ከጥቅምት 27 ጀምሮ ስደተኞች በሙሉ ከፍተኛ አስተዳደራዊ መግለጫ ማለት የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻና የፍች በብሔራዊ ባለሥልጣኖች ለመመዝገብ ችለዋል፡፡
ይህ አሠራር በኢትዮጵያ ወደፊት ለስደተኞች ጥበቃ የሚደረግ የልማት መሠረት ነው፡፡ ይኸውም በአገሪቱ ለስደተኞች በመሰጠት ላይ ያለው የሙያና ትምህርት ነክ መስፋፋት ከአጠቃላይ የስደተኞች አያያዝ መመርያ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ መመርያው በአገሪቱ የሚኖሩ ስደተኞች መሠረታዊ ፍላጎቶች ለመመለስ የሚያስችል ነው፡፡
በዜጎች ምዝገባ አሁን ባለው ሕግ ላይ የማሻሻያ ሃሳብ በማቅረብ ባለፉት አሥር ዓመታት በኢትዮጵያ የተወለዱት ከ70 ሺ የሚሆኑት ስደተኞች ከበፊት ጀምሮ የሚሠራ የልደት ምስክር ወረቀቶች ይሰጣቸዋል፡፡
ስደተኞችን በሚመለከት በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ሊተገብረው ከገባው ቃል መካከል፤ ለስደተኞች የሥራ ፈቃድ መስጠት፣ ለብዙ ስደተኞች ከስደተኞች ካምፕ ወጥተው ለመኖር መፍቀድና ለረጅም ጊዜ የቆዩት ስደተኞች ከአካባቢው ኅብረተሰብ ጋር መወሃሃድ እንዲችሉ መፍቀድ የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በአብዛኛው ከደቡብ ሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያና ከየመን የመጡ ከ883 ሺ በላይ ስደተኞችን ተቀብላ ታስተናግዳለች፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ