ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ኤርትራውያን ስደተኞች ቍጥር ጨመረ

ፎቶ፡ አለም አቀፍ የስደት ድርጅት (ኢንተርናሽዮናል ኦርጋናይዜሽን ፎር ማይግራንትስ IMO)

የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር (ARRA) እንደሚያሳየው በ2017 እ.አ.አ ከ20 ሺ በላይ  ኤርትራውያን ገብተዋል፡፡  ይህንኑ አኀዝ በ2016 እ.አ.አ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያን ብዛት ጋር እኩል ነው፡፡
አለም አቀፍ የስደት ድርጅት (ኢንተርናሽዮናል ኦርጋናይዜሽን ፎር ማይግራንትስ IOM ) ከ15 ሺ በላይ አዲስ ኤርትራውያን ስደተኞች ከመቀበያ ቦታ ወደ በሰሜናዊ ትግራይ ወደ እሚገኙት የሰፈራ ቦታዎች ማስገባቱ ይናገራል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ወኪል ከኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር (ARRA) እና ተባበሩት መንግሥታት ወኪል (UNHCR) ጋር ከአንድ ቦታ ከመነሳት በፊት የህክምና፣ የአስተዳደር፣ የመቀበልና የማጣራት በቅደም ተከተል የሚሠሩ ድርጊቶች ለአዲስ መጪዎች መጓጓዣ በማዘጋጀት በቅርበት ይሠራል፡፡
ካቲብ ካሊድ የአለም አቀፍ የስደት ድርጅት IOM የሽረ ቅርጫፍ ኃላፊ “በአሁኑ ጊዜ በአማካይ በየቀኑ መቶ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይፈልሳሉ፣ ይኸውም የሚያሳየው በ2017 እ.አ.አ በተከታታይ እየጨመረ የታየ ፍልሰት መሆኑን” ሲሉ ሃሳባቸው ገልፀዋል፡፡
“ከሰፈሩት ስደተኞች 50 % የሚሆኑት ዕድሜአቸው በ18 እና 24 መካከል የሚገኙ ወጣቶቸ ናቸው” ሲሉ ካሊድ ተጨማሪ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
በቅርቡ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት ወኪል (UNHCR) ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ 852,721 የተመዘገቡ ስደተኞች እያሏት 165,000 ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዳሏት ያሳያል፡፡