የአፍሪካ ስደተኞች የመን ውስጥ ጥቃት ገጥሟቸዋል

የፎቶክሬዲት፡ 2008 ቫይስ ኒውስ ቱናይት ኤችቢኦ – ቡራይካ የስደተኞች ማቆያ ተቋም የኤደን አስተዳደር – የመን.

በሚያዚያ 18 ሮይተርስ ለሂዩማን ራይትስ ዋች (HRW) እና UNHCR (የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ) ሪፖርት እንዳደረገው የመን የአፍሪካ ስደተኞች ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የአካል እና ጶታዊ ጥቃት ስለመኖሩ ከፍተኛ ማሰተንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

እንደ ቤል ፌደሪክ የሂውማን ራይትስ ዋች የስደተኞች መብቶች ዳይሬክተር ኤደን ውስጥ የስደተኞች ማቆያ ያሉ ዘቦች ወንዶችን በጭካኔ ደብድበዋል፤ ሴቶችን እና ወንድ ልጆችን በመድፈር በመቶዎች የሚቆጠሩትን በተጨናነቁ ጀልባዎች በመጫን ወደ ባህር እንዲሄዱ አድርገዋል፡፡

የየመን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ስላለው ሁኔታ ለሂውማን ራይትስ ዋች ጥያቄ የማዕከሉን ኮማንደሮች በማባረር ምላሽ ማድረጋቸውን እና ስደተኞች ወደሌላ ቦታ ማዘዋወር መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

የሂውማን ራይትስ ዋች እንደገለጸው ኤደን፣ ቡራይካ አካባቢ ያለው ማቆያ ማዕከል ከ2009 መጀመሪያዎቹ ጀምሮ በርካታ መቶዎች ኢትዮጵያውያን፣ ሱማሊያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የነበሩት ቢሆንም ከዚህ አመት መጋቢት ጀምሮ አብዛኛውን ኤርትራውያን የሆኑ 90 ስደተኞች ብቻ ቀርተዋል፡፡

ከዚህ በፊት ተይዘው የነበሩ ለሂውማን ራይትስ ዋች እንደገለጹት ተቋሙ በሰው የተጨናነቀ፣ ጽዳቱ የጎደለ እና ለሕክምና እንክብካቤ አነስተኛ አቅርቦት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ የምግብ አቅርቦት ቀጣይ ያልሆነ እና ዘቦች አልፎ አልፎ ምግብ የሚከለክሉበት ቦታ ነው ብለዋል፡፡

እዛ የተያዙት እንደገለጹት ዘቦቹ በመደበኛነት ሴቶች፣ ሴት ልጆች እና ወንድ ልጆች ላይ የጾታ ጥቃት ይፈጽማሉ፡፡ ተቋሙ ውስጥ የነበረች ኢትዮጵያዊ ሴት እንደገለጸችው ከ ዘብ ጋር የጾታ ግንኙነት ለማድረግ እምቢተኛ በመሆኗ በከባድ ሁኔታ ስለደበደባት በህመም እንደምትሰቃይ ገልጻለች፡፡ እሷ እንደገለጸቸው ሴቶች እና ሴት ልጆች በመደበኛነት እንደሚደፈሩ እና ሁለት ጓደኞችዋን ዘቦች ሲደፍሯቸው መመልከቷን ገልጻለች፡፡

UNHCR በጥይት የተመቱ፣ በመደበኛነት የተደበደቡ፣ የተደፈሩ አዋቂዎችና ህጻናት የደረሰባቸው ስቃይ፣በግድ ራቁት መሆን እና ግድያዎች እንዲመለከቱ የተገደዱ ምስክሮች እና የምግብ መከልከል በህይወት ከተረፉ ሰዎች ታሪክ ተጋርቷል፡፡

የስደተኞች ኤጀንሲ ለግዛቱ እና የግዛቱ ላልሆኑ ድርጅቶች የማቆያ ተቋማት አዲስ መጪዎች ሰብዓዊ በሆነ መልኩ መያዛቸውን ቁጥጥር እንዲያደርጉና እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል፡፡
ሂውማን ራይትስ ዎችበ ሰሜናዊ የመንን የሚቆጣጠሩትን የሁቲ ታጣቂ ቡድኖች በሆዲዳ ወደብ ከተማ ስደተኞችን ዝቅተኛ በሆነ ሁኔታ መያዛቸውንና ጥገኝነት እንዳያገኙ እና ጥበቃ እንዳይደረግላቸው በማድረጋቸው ይከሳል፡፡

ብዙዎች ስደተኞች ከአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህርን በማቋረጥ በየመን በኩል ሳውዲ አረቢያና ሌላ የገልፍ ሀገራት ስራ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ለህይወት አስጊ የሆነውን አደገኛ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡

TMP 17/05/2018