ኒጀር የሚያቋርጡ ስደተኞች ቁጥር እየቀነሰ ነው
የአውሮፓ መሪዎች ለኒጀር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ከገቡ በኋላ ኒጀርን የሚያቋርጡና ወደ ሊብያ የሚደርሱ የስደተኞች ቁጥር በጣም መውረዱ የዓለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት ዘገባ አስታውቋል፡፡
ዓለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት እንደሚለው በዋና የመተላለፍያ ኬላዎች የሚደረጉ አሰሳዎች በተለይ በምስራቃዊው ኒጀር ወደ ሊብያ የሚገቡ የስደተኞች ቁጥር ከ2016 መጨረሻ ጀምሮ በሚያስገርም ሁኔታ መቀነሱ ይገልፃል፡፡ ባለፈው ዓመት ከየካቲት እስከ ታህሳስ ወደ 292,000.00 የሚጠጉ ስደተኞች በኒጀር ከተማ ሰጉዲን በኩል አድረገው እንደተሻገሩ ሲታወቅ በዚሁ ዓመት ግን በሁለት ወራት ብቻ 8,700 ስደተኞች እንደገቡ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ አስታውቋል፡፡
በኒጀር የዓለም አቀፍ ስድተኞች ድርጅት ተልእኮ ዋና ሓላፊ ጁሴፔ ሎፕርቴ ለሮይተርስ እንደተናገሩት የስደተኞች ቁጥር በህገ-ወጥ የሰው አዛዋዋሪዎች ማቆያ ካምፕ በኒጀር – ኣጋዴዝ በጣም እንደቀነሰ ነው፡፡
“የስደተኞች ፍልሰት እንደባለፈው ዓመት አይደለም፤ ልናዋዳድረውም አንችልም፤ መንግስት ህገ-ወጥ አዛዋዋሪዎችን እያሰረና እየተከታተለ ነው፡፡ የጭነት መኪናዎችም እየወረሰ ከኒጀር ባህር በኩል ይወጣሉ ማለት አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በሊብያ ውስጥ የቆዩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩስደተኞች አስቀድመው በመግባታቸው ምክንያት ነው፡” ሲሉ የዳይረክተሪ ሪፖርት ይገልፃል፡፡
ባለፈው ዓመት ጀርመን ስድተኞችን ለመግታት ለኒጀር 77 ሚልዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡ የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ 610 ሚልዮን ዩሮ በእርዳታ መልክ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡ ጣልያንም ለኒጀር 50 ሚልዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡ በዓለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት የሚተዳደሩ የአውሮፓ ፈንድ በኒጀር አምስት ማእከሎች ለማቋቋም ተጠቅምበታል፡፡ይህም ስድተኞች የሚመገቡበት፣ መጠልያ የሚያርፍበትና ወደ ኣገራቸው መመለሳቸውና በዚህ ዓመት ደግሞ 1,500 ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ አለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት 2000 ስድተኞች ወደ ሃገራቸው ሸኝቷል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ