ኢትዮጵያ ፡ ኬንያና ታንዛንያ ህገወጥ ስደትን ለመግታት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የኢትዮጵያ ፣ኬንያና ታንዛንያ መንግስታት ስደትን በሚመለከቱ ጉዳዩች ላይ በጋራ ሆነው ለመስራት ተስማሙ። ሶስቱ መንግስታት ከመስራቅና ከአፍሪካ ቀንድ በመነሳት ወደ ደቡብ የሚደረገውን ህገወጥ ስደት ለመቀነስና በጉዞ ላይ ተይዘው መፈናፈኛ ላጡት ሰብአዊ መብቶችና አካላዊ ደህንነትን በመጠበቅ በተቀናጀ መንገድ ሊሰሩ ናቸው።
ስምምነቱ የተደረሰው ኪሚያዝያ 2 እስከ 4 2019 እ.ኤ.አ በዳርኤሰላም ታንዛንያ በተደረገው ተከታታይ ስብሰባ ሲሆን በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በተደረገው ድጋፍ የሶስቱ አገሮች የቴክኒክ ባለሙያዎች ተከታታይ ማሳስቢያ/ምክር ሰጥተዋል።
የእስር ቤቶች ሁኔታ እንዲሻሻሉና ከእስር ቤት ይልቅ ሌሎች አማራጮች እንዲኖሩ ጥሪ አስተላልፈዋል። እንዲሁም ስለ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ህገ ወጥ ሰደት የመከላከል እቅድና ስለ መመለስ የተመለሱትን ከሕብረተሰቡ ጋር የማቀላቀል ያሉትን ምርጥ ተሞክሮዎችን ውይይት አድርገዋል። ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሰደድ ይሞክራሉ። ያለ ህጋዊ ሰነድ በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ታንዛንያ ፣ ማላዊ ፣ ዛምቢያና ዙምባቤ በኩል ይጓዛሉ። ኣብዛኛው ጊዜ በህግ አካላት /ባለስለጣኖች ተይዘው ለእስር ይዳረጋሉ።
በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እና ስደተኞች በሚያቋርጡዋቸው አገሮች መንግሰታት ጋር በመሆን ያለ ረዳት የቀሩትን /መፈናፈኛ ያጡትን ኢትዮያውያን ስደተኞች ለመመለስ እየሰራች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በዳርኤሰላም ታንዛንያ ኤምባሲዋን ለመክፈት በመወሰንዋ ያላቸው አድናቆት በመግለፅ የታንዛንያ የአገር ውስጥ ሚኒስተር ካንዚሉ ጎላ “ኤምባሲው ከተከፈተ ጀምሮ በታንዛንያ በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩትን 301 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል “በማለት ተናግረዋል።
“የኢትዮጵያ ኤምባሲና የታንዛንያ የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት በጋራ በመሆን የህገወጥ ስደተኞችን ጉዳይ በሚመለከት የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ያመለክታል” በማለት አክለው ተናግረዋል።
ቃሲም ሱፊ በታንዛንያ የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ተልእኮ ዋና ሃላፊ ሲሆኑ አገራቱ ህገወጥ ስደትን ለመግታት የሚያደርጉትን ትብብር በማድነቅ “እርዳታ ሰጪ/ ለጋሽ ማህበረሰብ ለአደጋ የተጋለጡትን ስደተኞች ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድና ወደ ነበሩበት ሕብረተሰብ ለማዋሀድ እርዳታቸውን እንደሚቀጥሉ ተሰፋ አለኝ” በማለት ተናግረዋል።
ህገወጥ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ከፍተኛ ጥረት የመነጨው ምስጢራዊ በሆነ ጉዞ ምክንያት የሚደርሰው ፋይናንሳዊና አካላዊ ጉዳት የሚደርስባቸው ብዙ ስደተኞችን ከመርዳት ጋር የተያያዘ ነው። ስደተኞች እንደተለመደው ዋስትና ለሌለውና መሳካቱን ለማያስተማምን ጉዞ ከፍተኛ ገንዘብ ለህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች መክፈል አለባቸው።
ብዙ ስደተኞች በሚያደርጉት የስደት ጉዞ/ሙከራ ህይወታቸውን ያጣሉ። ባለፈው ዓመት ወርሐ ጥቅምት ላይ 13 ሰዎችን በመያዝ በታንዛንያ የባህር ጠረፍ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ የነበረች ጀልባ በመገልበጥዋ ምክንያት ሰባት ኢትዮጵያውያን በውሃ ሰጥመው ሞተዋል።
TMP – 17/04/2019
ፅሑፉን ያካፍሉ