በህገ ህገወጥ መንገድ በስደት ታንዛንያ የገቡት ኢትዮጵያውያን ድሰተኞች ወደ ኣዲስ-ኣበባ ተመለሱ

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ኣፍሪቃ ለመግባት ለማቅናት ታንዛንያ ለገቡት 67 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እገዛ እንዳደረገ የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት አስታውቀል።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር ስደተኞችን ከእስር ቤት በማስለቀቅና አስፈላጊ የሆኑትን የጉዞ መረጃዎችና ማስረጃዎችን በመስጠት ወደ አዲስ አበባ ለመግባት እንዳስቻላቸው ዳሬሰላምን ከመልቀቃቸው በፊት እግረ መንገዳቸው የህክምና የምርመራና የአልባሳት ስጦታ እንደተደረገላቸውም ጨምሮ ገልፃል። 67 ስደተኞች በሙሉ መስከረም 28/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ እንደደረሱ ታውቃል።

እነዚህ በፍቃዳቸው ከስደት የተመለሱት ሰዎች ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉና ወዴት መሄድ እንደሚፈልጉም ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል፡፡ እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ ከስደት ተመላሾቹ የእያንዳንዱ ተመላሽ መሰረት በማድረግ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለማጋናኘት እገዛ በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚደረግላቸውና ወደ ሚቀላቀሉት ማህበርሰብ የተቀላጠፈ እንደሚሆን ጨምሮ ገልፀዋል።

በሰሜኑ ክፍል ወደ አውሮፓ ከሚደረገው ጉዞ በተጨማሪ ወደ ደቡባዊ ክፍል ወደ ደቡብ አፍሪቃ መጓዝ ተመራጭና ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱ ታውቃል። በጥር 2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ የአፍሪቃ ሕብረት የአፍሪቃውያን ነፃ እንቅስቃሴ በመላው አፍሪቃ አህጉር የሚፈቅድ ፕሮቶኮል መፈረሙን ይታወቃል። ስምምነቱም እንዲተገበር ቢያንስ 15 ሃገሮች ማፅደቅ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን ታንዛንያ በተለየ ከአቅጣጫ መተግበሯና ወደ ሃገርዋ ለሚገቡ ዜጎች ከተለያዩ ሃገራት ወድያውኑ አገሯ እንደገቡ የቪዛ ቅጽ ብላ አማራጭ እንደምታደርግ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከናጀርያና ጅቡቲ ለሚገቡ ስደተኞችም ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች። ወደ ታንዛንያ ለመግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የቪዛ ማመልከቻዎቻቸው ከ3 ወር በፊት አስቀድሞ ጥያቄ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከታንዛንያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የተደረጉት የመጀመሪያዎቹ አይደሉም።

ባለፈው ሰኔ ወር የአለም አቀፍ የስደት ተመላሾች ድርጅት ከታንዛንያ ጋር በመተባበር 300 ህገ ወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተለያዩ የታንዛንያ የእስር ቤት ማእከላት ተይዘው የነበሩትን አስለቅቋል፡፡

በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሄድ በኬንያ ፣ ታንዛንያ ፣ ዛምብያና ዝምባብዌ በኩል የተሻለ እድልና ኑሮ ፍለጋ ረዥሙን የየብስ ጉዞ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ ይህንን ጉዞ ሲያደርጉ ደግሞ በጣም ብዙ ገንዘብ ለደላሎች እንደሚሰጡና መድረሳቸውም እንደማያረጋግጡ ለመሸጋገር ሲሉ በድንበር ጠባቂዎችና የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣናት ሲያዙ ደግሞ የመጨረሻ እጣ ፈንታቸው እስር ቤት መግባት ይሆናል፡፡

TMP – 19/10/2018

ፎቶ አይ.አ.ኤም። ኢትዮጵያውያን በጁልየስ ኔሬሬ. አለም አቀፍ አውሮፕላን ማርፋያ ፡ዳሬሰላም