ሃንጋሪ ብዙ ስደተኞች ለመቀበል እንደማትፈልግፍ አስታወቀች

ምንጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የንግድ :- ፎቶ ሮይቶርስ
ሃንጋሪ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለመተባበር ዝግጁ አለመሆኑዋና የፖለቲካ ጥገ”ነት ጠያቂ ስደተኞች መጠሊያ እንደማትሰጥና በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን የፖለቲካ ጥገ”ነት ስደተኞችን ወደ መላው የህብረቱ አባል ሃገራት ለማከፋፈል የወጣውን እቅድ እንደማትቀበል አስታውቃለች፡፡
የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፒተር ስዝርቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ሃንጋሪ በስደተኞች ላይ ያላት አቋም ግልፅና የማያሻማ የማያወላውል ነው፤ ህገወጥ ስደት አደገኛ ነው ፤ በህገወጥ ስደት ምክንያት አውሮፓ አሁን እየታየ ያለዉን የሽብር ጥቃትና የሽብርተኝነት አደጋ እያጋጠማት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረው በአፅንኦት እንዳስረዱት ማንኛውም የስደኞችን ፍልሰት የአውሮፓ ፍላጎትን የሚፃረር ነው ብለዋል፡፡

በስደተኞች እንደገና መስፈር /ማስተናገድ/ እቅድ የአውርፓ ኮሚሽን በስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች የየአገሮቹ ድርሻ ቁጥር /ኮታ/ ይወሰናል ተብሏል፡፡ ይህም ከአቅም በላይ ስደተኞችን እያስተናገዱ ያሉት ሃገሮችን ጫና ያቃልላል ተብሏል፡፡
በ2015 የአውሮፓ ህብረት መሰረት 160000 ስደተኞች ከግሪክናከጣልያን ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች እንደየ ኮታቸው/ድርሻቸው/ ለማስፈር በተደረሰው ውሳኔ መሰረት በሁለት ዓመታት ውስጥ እንዲከናወንመወሰኑ ይታወቃል፡፡ ከሕዳር ወር 2017 ጀምሮ ወደ 32000 የሚጠጉ ስደተኞች እንደተመደቡ ይታወቃል፡፡
የማስፈር ስራውን እቅድ ለስድተኞች አመቺ ባልሆኑ አገሮችተቃውሞ ሲደርሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሃንጋሪና ፖላንድ በዚሁ እቅድ እንደማይካተቱና ስሎቫክያን ግን ጥቂት ስደተኞች ከግሪክ መቀበሏ ይታወቃል፡፡