ትርጉም አርእስት፡- የሊብያው ጀነራል አገሪቱን ለመረጋጋትና ስደተኞችን ወደ አውሮጳ እንዳይገቡ እንዲያቆሙ አስታወቀ

ቀን  3 ጥቅምቲ 2017

የሊብያ ብሄራዊ ጦር ኮማንደር የሆኑት ጀኔራል ከሊፋ ሃፍታር አገሪቱን ለማራጋጋት  የጦር ሃይል እንዲጠቀሙ ያስታወቁ ሲሆን፤ ይህንንም ለማድረግ የፖለቲካ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግ ሳይጠቁሙ አላለፉም፡ ሊብያ የማሓመድ ጋዳፊ አገዛዝ ከተገረሰሰ ከ2011 ጀምሮ ያልተረጋጋችና ለሰው ልጅ ኑሮና ደህንነት አስቸጋሪ አገር መሆንና በዚህም ሳብያ የድህንነት ስጋትና ህገ ወጥነት እንዲሁም የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብ እየሰፋ እየጠነከረ መምጣቱና ይህም በመቶ ሺዎች የሚቀጠሩ ስድተኞች በጣልያን በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ  ለማሻገር ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ እንደሚጓዙ  ታውቋል፡፡ይሁን እንጂ በቅርቡ በአውሮጳ ህብረትና በጣልያን መንግስት ትብብር  የህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች መረብ እየበጣጠሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ የሊብያው ጀኔራል ሃፍታር ለጣልያን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት “ ሽብርትኝነት በሊብያ ውስጥ እያሸነፍነው እንገኛለን፡፡ ይህ በዲፕሎማሲው መንገድ ሳይሆን በጦር መሳርያ በተደገፈ ስራ መሆኑ ገልፀዋል፡፡” ጀኔራል ሃፍታር ጨምረው እንደገለፁት “  የጣልያን የመከላከያ ሚኒስተር ሮቤርታ ፒኖቲ የሊብያ ወታደሮች ለማሰልጠን እንደተስማሙና ይህም የተባበሩት መንግስታት የጦር መሳርያ ማዕቀብ  እንዲቀጥልና ይህም የአውሮጳ አገሮች ስደተኞችን ለመመለስ /ለማቆም/ ፍላጎት ካሳዩ ነው ብለዋል፡፡

ጀኔራሉ ጨምረው ሲናገሩ የአገራቸው ጦር ሃይል ስደተኞችን ወደ አውሮጳ እንዳይገቡ ለማቆም ያለው ችሎታ አድንቀዋል፡፡ በደቡብ ዳርቻ ለሚደረገው የጠረፍ ቁጥጥር የሰው  ሃይል ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸው ሲገልፁ ነገር ግን የአውሩፓ አገሮች እርዳታ እንደሚያስፈልግ ፤ይህም እንደ ሰው አልባ አውሮፕላን፤ ሄሌኮፕተሮችና የምሽት ቅኝት የሚያካይዱ መሳርያዎችና መኪናዎች እንደሆኑ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የታጠቁ ቡዱኖችን በመደገፍና ፀረ ህገ ወጥ አዛዋዋሪዎችና ፖሊሶች እንዲሆኑ የሚያደርገውን የጣልያን ስራዎች ኮንነዋል፡፡ የጣልያን መንግስት በሚሊሻዎች መመራት የለበትም ፤ ይህም በጣም ትልቅ ስህተት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ብዙ ሚድያዎች የአናሶ አስዳባሺ ብርጌድ መሪ የሆነው ግለሰብ በሌላ ግዜ ከጣልያን መንግስት የስድተኞች ጀልባዎችን በማስቆም እንደተቀበለና ይህም የጣልያን መንግስት እንዳስተባበለ ታውቋል፡፡ የስደተኞች ቁጥር በእጅጉ እንደቀነሰና ይህም ወደ ጣልያን አገር ጠረፍ ይጎርፍ የነበሩትን ስደተኞች የአናሳ አስዳባሺ ቡዱኖች ከተበታተኑ ከሓመሌ ወር ወዲህ ሲሆን ይህም የስራ እድል ለማግኘትና እውቅና ለማግኘት የተደረገው ተስፋ መስጠትዋ መሆኑ ታውቋል፡፡