የሜዲቴራንያን ባህር ለሚሻገሩት ስደተኞች በማስመሰል የተሠራ የማይረባ ሕይወት ማዳኛ ጃኬት ተሸጠላቸው

ፎቶ፡ ሳይሞን ለዊስ .በአፍሪቃ አደገኛና አስመስሎ የተሠራ “ሕይወት አድን ጃኬቶች” ለስደተኞች በመሸጥ ላይ ነው፡፡

በሊቢያ በሰዎች ላይ የሚነግዱ ኮንትሮባንዲስቶች በማስመሰል የተሠራ የማይረባ ሕይወት ማዳኛ ጃኬት እየሸጡ የስደተኞች ሕይወት እያጠፉ ነው፡፡

አፍሪቃውያን ስደተኞችን በሜዲቴራንያን ባህር ለማስተላለፍ በርካታ ገንዘብ የሚጠይቁት አስተላላፊዎች፣ ይህንኑ ዋጋ የሌለው ሕይወት የማያድን ጃኬት በውድ ዋጋ በመሸጥ ብዙ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡

የአስተላላፊዎቹ የማጭበርበር ሥራ ስደተኞችን ለሞት የሚዳርግ ነው፡፡ ጃኬቶቹ በርካሽ አረፋ/ ፎም የተሠራና ለባሹ በውሃ ውስጥ ቢጠልቅ እጅግ በጣም ክብደት ይጨምርና ለባሹን በማእበሉ ይጎትተዋል፡፡

የሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ጋዜጣ አዘጋጅ፣ ሳይሞን ለዊስ አንድ ሰው በአለም ጥሩ ዋናተኛ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በሚንጠባጠብ ጃኬት ለብሶ መዋኘት አይችልም፤ እሆነ ያለውም ይህ ነው ብሏል፡፡

“የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ከማንኛውም አንድ ስደተኛ ወደ የሚሞትበት ቦታ ከመሄዱ በፊት ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በማወቅ ረገድ በጣም ብልጦች ናቸው፡፡ ስለ ሕይወት ምንም ደንታ የላቸውም፣ የሚያውቁት ሰዎችን እንደ ከብት ማጐርና ገንዘብ ማግኘት ብቻ ነው” ብሎ ለዊስ ይገልፃቸዋል፡፡