የአውስትርያ ፓርቲዎች ሃይለኛ የስደተኞች የፖሊስ ሃሳብ አቀረቡ

ፎቶ ቢዝነስ፡- ኢንሳይደር የፖሊስ የኒኮልሰደርፍ የድንበር አከባቢ ሊየቋርጡ ሲሞክሩ በህግ ስርዓት ሲያስከብር (በማስከበር ስራ
ላይ እያለ)

አዲሱ የአውስትርያ የጥምር መንግስት ከግራ ዘመምና ከቀኝ አክራሪ የነፃነት ፓርቲና የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ነው
የተመሰረተው፡፡ ይህ መንግስት ሃይለኛው የስደተኞች የፖሊስ ሃሳብ ለውሳኔ ማቀረቡ ታውቋል፡፡

ይህ የተነደፈወ አዲሱ የስደኞች የፖሊሲ ሃሳብ የስደተኞችን ማንነት ለመለየት እንዲያግዝ ተብሎ የፀጥታ ሃይሎች ወደ
ሃገሪቱ ሲገቡ የያዘዋቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንደነ ሞባይል ቆፎዎች የመሳሰሉት እንዲነጠቁ ፣ በእጃቸው
የተገኙ ገንዘቦችም እንዲወረሱ የሚያደርግ ሲሆን ይህም ለአንዳንድ አዳዲስ ገቢዎች ስደተኞች ወጭዎች መሸፈኛ
እንዲውልና ለሃገሪቱ ምንም ዓይነት የገንዘብ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ ከመንግስት የሚያገኙትን የገንዘብ ድጋፍ
የሚያስቀር መሆኑ ታውቋል፡፡
የገዢው ፓርቲዎች አባላት ይህንን ሕግ ያረቀቁት በ180 ገፆች ላይ በሰፈረው የጋራ ሰነድ መሆኑ ታውቋል፡፡

የስደተኞችን ጥቅማጥቅሞች የሚቀንሱበት አሰራር አዲሱ ቻንስለር ሰባስቲያን ኩርዝ ሲያብራሩ “በሃገሪቱ ምንም
ዓይነት ስራ ሳይሰሩና ለሃገሪቱ ምንም ዓይነት ግብር (አስተዋፅኦ) ለማያበረክቱ ስደተኞች በሺዎች የሚቆጠሩ ዩሮና
ጥቅማ ጥቅሞች ማግኘት አይገባቸውም ምክንያቱ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የለምና” ብለዋል፡፡
“ይህ የፖሊሲ ለውጥ በሚቀጥሉት 5 ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን እኛም አጥብቀን ኣጥብቀን የምንፈልገው ሕግ
ነው፤ ግባችንን ግልፅና የማያሻማ ነው፤ የኣገሪቱ ዜጎች /ግብር ከፋዮች/ እፎይታ እንዲያገኙ እንፈልጋለን፡፡ በዓለም ላይ
ያለንን ቦታ እናጠናክራለን፤ የማህበራዊ ዋስትናችንም እናረጋግጣለን፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሃገራችን ድህነነትና ፀጥታ
ዘብ እንቆማለን ፤ ይህም ሕገ -ወጥ ስደትን በመታገል መሆኑ “ሓላፊው ጨምረው ይገልፃሉ፡፡

በሚኒስትሮች ደረጃ ያሉት ቦታዎች (ሹመቶች) የሃገር ውስጥ ጉዳይ ፣ የመከላከያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመሩት
በፍሪደም ፓርት መሆኑ ጨምረው ገልፃል፡፡ይህም ማለት ደግሞ የስደተኞች ጉዳይ፤በመጠልያ የሚገኙ ተገን ጠያቂዎች
ጉዳይና የወንጀልና ኣሸባሪነት ስራ መቆጣጠር በፓርቲው አመራሮች ስር መሆኑ ያመለክታል፡፡ ይህም ጥብቅ የሆነ
የቁጥጥር ስራ በተለይም በስደኞች ወደ ሃገሪቱ በሚገቡ ሰዎች ጠበቅ ያለና ከክርስቲያን ዲሞክራቲክ የባሰ እንደሚሆን
ታውቋል፡፡

አዲሱ የአውስትርያ መሪ በግልፅ እንዳስቀመጡት የኣውሮፓ ህብረት ስድተኞች የመቀበል ኮታ/ድልድል/
እንደማይቀበሉትና ከነሃንጋሪና ፖላንድ ጋር ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ገልፀዋል፡፡

ቻንክለር ኩርዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያሉም የህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ሃገሪቱ መግባት አጥብቀው ይቃወሙና
ይታገሉ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ ይህም ከባልካን አገሮች ለሚገቡ ስደተኞች ለመከላከል አውስትርያ ከሚያዋስንዋት
የባልካን አገሮች ድንበር መዝጋቷ ይታወቃል፡፡
ይህም ተግባር ደግሞ ሁሉም የእውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የማእከላዊው ሜዲተራንያንን በመዝጋት እንዲጋሩትና
እንዲተገብሩት ለማሳመን እንደሚሞክሩ ገልፀዋል፡፡