ኢትዮጵያን ስደተኞች በግድ ወደ ባህር እንዲገቡ በመደረጋቸው ሳይምቱ እንዲለቁ ተነገረ

ፎቶ ክረዲት አይ.አ.ኤም የአፍሪቃ ስደተኞች በአይ.ኦ.ኤም በ2015 ከሞት ዳኑ

22 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ዳርቻ ጠረፍ በሃይል ወደ ባህር እንዲገቡና እንዲጓዙ ስለተደረጉ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ በተባበሩት መንግስታት /የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት / ኣይ.ኦ.ኤም ተገልፇል፡፡ እነዚህ ደብዛቸው ሊጠፉ የቻለዉ በተከታታይ በየመን የባህር ጠረፍ አቋርጠው ወደ ሜዲትራንያን ባህር በመሻገር ወደ አውሮፓ በሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጉዘዎች መሆኑና አደገኛ የጉዞ መስመር በመሆኑ ነው፡፡

የአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ዳይሬክተርና የኦፕሬሽንና የአስቸኳይ እርዳታ ሃላፊ የሆኑት መሓመድ አብዲቀር በቲዊተር ገፃቸው እንደገለፁት አራት ጀልባዎች ላይ ተሳፍረው የነበሩና ከሶማልያ ጠረፍ የመጡት እዛው ባህር ዳርቻ ከመድረሳቸው በፊት ከጀልባ ወርደው ሻብዋ ክፍለ ሃገር ከተማ ሲደርሱ በዋና እንዲሻገሩ ስለተደረጉ ዋና የማይችሉት ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ገልፀዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ቃል ኣቀባይ በጀኔቫ በሰጡት መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስረዱት “በጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ስደተኞች ባህር ዳርቻ ሲደርሱ ወደ ጥልቅ ባህር ተወርውረው በዋና እንዲኛገሩ ስለተገደዱና ከነዚህም ውስጥ 22 ኢትዮጵያውያን የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልፀዋል፡፡ “ወደ ዝርዝር መግለጫ ግን አልገቡም፡፡
“በየመን የፀጥታ ሁኔታ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም አሁንም የስደተኞች መተላለፊያ መሆኑና ይህንን ዓይነት ዘገባ በተደጋጋሚ መስማት ቀጥለዋል ብለዋል፡፡”

ወደ 600 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሴቶችና ወንዶች በጀልባዎች እንደተሳፈሩ ሚልማን ሲገልፁ ይህም በርካታ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በአንድ ግዜ ሻብዋ በተባለችው የባህር ዳርቻ ከተማ ሲደርሱ ይህ ለመጀመርያ ግዜ መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት እንደተገለፀው ከሆነ ወደ 87,000 ሰዎች በ2017 ከአፍሪቃ ቀንድ ተነስተው የመን እንደደረሱ ታውቋል፡፡
የተ.መ.ድ.ኤጀንሲዎች ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ለሚነሱ ስደተኞች ስለጉዞው አስቸጋሪነትና አደጋው ቢነገራቸውም ሰሚ ጀሮ አልተገኘም፡፡

ባለፈው ወር በየመን ባህር ጠረፍ አንድ ጀልባ በመስመጡ 30 አፍሪቃውያን ስደተኞች እንደሞቱ ታውቋል፡፡ የአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችና ደላሎችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ይህም “ያልተገባ ገንዘብ ለማካበት” ሲሉ አደጋ ውስጥ እንደሚቷቸው እና ጀልባዎቹ ሲገለበጡ የመሳርያ ተኩስ እንደሚሰማ እማኞች ተናግረዋል፡፡

የ.ተ.መ.ድ ኤጀንሲዎች በየመን ያለው የተራዘመ ጦርነት ስደተኞችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ ድንገተኛ ሞትና እስር ፣ ህገ-ወጥ ዝውውር እና ስደተኞች እንዲባረሩ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡