አንድ የሊቢያ ጀልባ በጠረፍ አካባቢ በመገልበጡ ከ30 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሞቱ

ፎቶ፡ ሮይተርስ. የሙት ስደተኞች ሬሳዎች ከባህር ወጥተው ወደ ሊቢያ ሲመለሱ

ሁለት የሊቢያ ጀልባዎች በመገልበፃቸው ከ30 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በጠረፍ አካባቢ በምትገኘው በጋራቡሊ ከተማ በ25 ሕዳር (በፈ.አ) መሞታቸው የሊቢያ ባሕር ኃይል ገለፀ፡፡

የሊቢያ የጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ ኰሎኔል አቡ አጃላ ዓብደል ባሪ፣ ጠባቂዎቹ ከአንድ ጀልባ ፣ 31 ሬሳና 60 ከሞት የተረፉ ሲገኙ፣ ኩለተኛው ጀልባ ድግሞ 140 ተጓዦች መትረፋቸው ተናገረ፡፡ አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ ጣልያን አገር ለመሻገር የመጡ አፍሪቃውያን ነበሩ፡፡

ኰሎኔል አቡ አጃላ የመጀመርያዋ የውድድር አነስተኛ ጀልባ እነሱ ከመድረሳቸው በፊት ናት የጠለቀችው ብሏል፡፡ በተጨማሪ የጠረፍ ጠባቂዎች እንድ እነድ የስቃይ ምልክት እንደ ሰሙ ወደ ቦታው ሄደው የተመለከቱት ሰዎች በጀልባ አካል አካባቢተንጠልጥለው የቀሩት ደግሞ ሞተው ማየታቸው አቡ አጃላ ተናግሮኣል፡፡

የሊቢያ ባህር ኃይል ቃል አቀባይ አዩብ ቃሲም ከሟቾቹ መካከል 18ቱ ሴቶች፣ ሦስቱ ደግሞ ህፃናት መሆናቸውና 40 የሚያህሉም መጥፋታቸው ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነግሮአቸዋል፡፡

ሊቢያ የጥበቃ ጀልባ አዛዥ የሆነው ናስር አልጋሙዲ የዳኑ ሰዎች እንዳሉ ለመፈለግ ከአምስት ሰዓት በላይ እንደሠሩና አንዲት ሴት ጩኸቷን ሰምተን ሄደን አድነናታል ብሏል፡፡

ከሞት የተረፉት ስደተኞች ወደ ሊቢያ ባህር ኃይል ካምፕ ተወስደዋል፡፡

በአለም አቀፉ የየስደተኞች ድርጅት (IOM) ሪፖርት መሠረት በ2000 እና 20017 መካከል ቢያንስ 33000 ሰዎች መሞታቸውና የሜዲተራንያን ባህር በዓለም ስደተኞችን የሚገድል ባህር ነው በማለት ገልፆታል፡፡ –