የአውሮፓ ህብረት በባህር ላይ ሞትን ለመቀነስ ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሊቢያ ወደብ ለማሰልጠን አቅዷል

በሬውተርስ ሪፖርት መሰረት የአውሮፖ ህብረት ተልዕኮ በሜድትራኒያን ላይ በ2010 መጨረሻ እስከ 500 ተጨማሪ የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎችን ለማሰልጠን አቅዷል፡፡
የባህር ላይ ተልዕኮ ስያሜው ‹‹ኦፕሬሽን ሶፊያ›› ፈጣን በሆነ ሁኔታ ስደተኞች ወደ ጣልያን መሄዳቸውን ለመቀነስ
እና የባህር ላይ ሞትን ለመቀነስ የሊባውያን ወደብ ጠባቂዎችን ለማሰልጠን አቅዷል፡፡
በ6/7/2010 ከቱኒስ የአውሮፓ ህብረት ናቫል ተልዕኮ በሜድትራኒያን ኃላፊ የሃኑት ሬር አድሚራል ኤነሪኮ ክርዴንዲኖ እንደተናገሩት በሳቸው ተልዕኮ የሰለጠኑ 138 ሊቢያውያን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የባህር ማቋረጥን ቁጥር ለመቀነስ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎች ከ2009 አጋማሽ ጀምሮ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡
እሳቸው በተጨማሪም እንደገለጹት በ2009 ሊቢያውያን 18,000 ያህል ህይወት አድነዋል፡፡ በ2007 800 ብቻ በንጽጽር የነበሩ ቢሆንም የአውሮፖውያን የበጎ አድራጎት ሰዎችን የማዳን ድርጅት የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎችን በሰዎች ማዳን ወቅት ባላቸው ተገቢ ያልሆነ ባህሪ እና አልፎ አልፎ ስደተኞችን ህይወት ስጋት ላይ በመጣላቸው ይከሳል፡፡ ከዚህ አኳያ የወደብ ጠባቂዎቹ ክሱን ክደዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ፓናል ኤክስፐርቶች የቅርብ ጊዜ ክሶች ሰዎችን የሚያዘዋውሩ እና በወደብ ጠባቂዎች መካከል ግንኙነት አለ የሚል ሲሆንም ክሬዴንዲኖ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡
በባህር ላይ ወታደራዊ ወደብ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ ዮኒፎርም ያደረጉ ሚሊሺያዎች ተመሳሳይ ጀልባዎችን የሚጠቀሙ አሉ፡፡
የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎችን ባህር ላይ ቁጥጥር አድርገናል፣ አውሮፕላኖች አሉን የሚከታተሉ መርከቦች አሉ
በየወቅቱ ስብሰባ እናደርጋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከ130 በላይ ሰዎችን አሸጋጋሪዎች ባህር ላይ ታስረዋል፡፡ ለጣሊያን ባለሥልጣኖችም ቀርበዋል፡፡ ሆኖም ሊቢያ ውስጥ ያለውን የሰዎች አሸጋጋሪ ኔትዎርክ ለማስተጓጓል ቀላል አልነበረም፡፡ ሊቢያም ከአለም አቀፍ ባለሥልጣናት
ውጪ ሰዎችን የማሸጋገር ስራ ቀጥሏል፡፡
ክሬዲንዶ እንደተናገሩት ከበርካታ አለም አቀፍ አክተሮች፣ ኢንተርፖል፣ ዮሮፖል፣ ፍሮንቴክስ ጋር የምንሰራ ሲሆን ምስልን እየሳልን ቢሆንም ምዘናዎች ለማድረግ ገና አልተቻለም፡፡
ኦፕሬሽን ሶፊያ በ2007 በአውሮፓ ህብረት የሰዎችን መሸጋገር ለማስቀረት የተጀመረ ሲሆን ከ2008 ጀምሮ የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎችን እያሰለጠነ እና እያስታጠቀ ነው በሐምሌ 2009 የአውሮፓ ህብረት ተልዕኮው እንዲቀጥል እና
እስከ 2010 መጨረሻ እንዲፈጽም እድሳት አድርጓል፡፡
እንደሬውተርስ ዘገባ በጣሊያን ናቪ ከተደመሰሱት ውጪ ኦፕሬሽን ሶፊያ እስካሁን ከ500 በላይ የሰው አሸጋጋሪ ጀልባዎችን በመያዝ ደምስሷል፡፡