የአፍሪካውያ ስደተኞች ሬሳ በሞሮኮ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ተገኘ
አብዛኞቹ ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ከ 20 በላይ ስደተኞች ሬሳ በፈረንጆቹ የካቲት 3 በሞሮኮ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ተግኝቷል፡፡ የስፔን መርከበኞች ሬሳዎቹን ከተመለከቱ በኋላ ለሞሮኮና ለስፔን ነፍስ አድን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ከሞሮኮ ጋር በድንበር የምትዋሰነው የስፔንዋ ሜሊላ ግዛት ቃልአቀባይ እንዳሉት 20 ሬሳዎች የተገኙት በሞሮኮ የውሃ ግዛት ላይ ሲሆን፤ የስፔን ፖሊስ የቅኝት ጀልባ ደግሞ ተጨማሪ አንድ ሌላ ሬሳ ያገኘ ሲሆን ወደ ሜሊላ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡
አንድ የህክምና ሃላፊ ለ AFP እንደተናገሩት፤ ከተገኙት ሬሳዎች መካከል ሶስት ሴቶች የነበሩ ሲሆን በኋላ ላይ በሞሮኮዋ የ ናዶር ከተማ ወደሚገኝ የመቃብር ቦታ ሰወስደዋል፡፡
“የሞቱት 21 ሰዎች በትንሽ ጀልባ ተጭነው ወደ ሜሊላ እየተጓዙ ነበር” ብለዋል ዎኪንግ ቦርደርስ የተባለው እርዳታ ድርጅት ባልደረባ የሆኑት ኤለና ማሌኖ በትዊተር ገፃቸው ላይ፡፡ በተጨማሪም የተጓዦቹ አጠቃላይ ቁጥር ከዚህ በላይ ቢሆንም “እስካሁን ድረስ ይህን ማረጋገጥ የሚችል ከአደጋው በሂወት የተረፈ ሰው አልተገኘም” ሲሉ አክለዋል፡፡
ከዚህ ክስተት ከአንድ ቀን በኋላ፤ የስፓኒሽ እና የሞሮኮ ነፍስ አድን ቡድኖች የጠፉ ተጨማሪ ሰዎችን ለመፈለግ በአየር እና በባህር በድጋሚ ቅኝት አድርገዋል፡፡
እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ፤ ስደተኞች የስፔን ይዞታዎች ወደሆኑት የሜሊላ ግዛቶች ለመግባት የየብስ ጉዞ ነበር የሚያደርጉት፡፡ በነዚሁ ግዛቶች ላይ የስፔን ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጥበቃ በማጠናከራቸው፤ በርካታ ስደተኞች ወደነዚሁ ግዛቶች ለመግባት ሜዲትራንያንን ለማቋረጥ እየሞከሩ ነው፡፡
ከዚህ በፊት፤ ብዙ ስደተኞች የሜሊላ አጥርን ለመዝለል ነበር የሚሞክሩት… አሁን ግን፤ ጠንካራ ቁጥጥር ከተደረገ በኋላ ግን በባህር ብቻ ነው አቋርጠው መግባት የሚችሉት” ብለዋል የሞሮኮ ሰብአዊ መብቶች ማህበር ሃላፊ የሆኑት ኦማር ናጂ ለ AFP ሲናገሩ፡፡
ስደተኞች ይህን የባህር ጉዞ ለማድረግ እያንዳንዳቸው 3,000 ዩሮ ለህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች መክፈል ይጠበቅባቸዋል፤ ይህ የሰዎች ዝውውር የሚደረገው ደግሞ በባለስልጣናት አፍንጫ ስር ነው” ሲሉ ጨምረዋል፡፡
ስደተኞች በሊቢያ የሚገጥሟቸው አደገኛ ሁኔታዎች ስደተኞች በሰሜን አፍሪካ እና የስፔን ደቡባዊ የየብስ ግዛት መካከል ባለው ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት እንዲሞክሩ እየገፋፏቸው ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት የስደት ጉዳዮች ኤጀንሲ እንደሚለው፤ በፈረንጆቹ 2018 የመጀመርያው ወር ላይ ከ 243 ሰዎች በሜዲትራንያን ባህር ላይ ሞተዋል አሊያም የገቡበት አልታወቀም፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ