የአፍሪቃ ስደተኞች ተራሮችን አቋርጠው ወደ ፈረንሳይ ለመጓዝ ሊሞክሩ ሲሉ ህይወታቸው እያለፈ ነው፡፡

ፎቶ ፡-ስደተኞች የአልፓስ ተራሮችን ለማቋረጥ ሲሉ በበረዶ የተሸፈኑ የበረዶ ክምሮችን በማቋረጥ ከጣልያን ወደ ፈረንሳይ ሃገር ለመግባት ሰሜን ጣልያን የምትገኘው የባርንዶንቺያ ከተማ ለመግባት ሲጓዙ ታሕሳስ 21 ቀን
የበደረሶ ክምሮችን በፀደይ ወራት መቅለጥ በሚጀምሩበት ጊዜ የፈረንሳይ የነፍስ አድን ሰራተኞች የአልፕስ ተራሮችን ለማቋረጥ የሚሞክሩ የአፍሪቃውያን አስከሬኖች እንደሚያገኙ ይገምታሉ፡፡
እንደ ነፍስ አድን ሰራተኞች ገለፃ በየቀኑ ከ10 እስከ 12 ሰዎች /ስደተኞች/ ከጣልያን ወደ ፈረንሳይ ለመግባት ይሞክራሉ፡፡ ግማሾቹ ባዶ እግራቸውን ፤ የሙቀት መጠኑ /የቅዝቃዜው መጠን/ ከዜሮ በታች -20 ሲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነበትና ሃይለኛ በረዶ ባለበት ወራት ማለት ነው፡፡ አንድ አፍሪቃዊ ሰው /ሰደተኛ/ ከተራራው አናት ላይ ወድቆ ተከሰከሰ፡፡ ባለፈው ሳምንት አንድ ሞተ፡፡ ይኸውም ወደ ጥርጊያ መንገድ ለመግባት ተጠልሎበት ከነበረው ቦታ ወድቆ መሞቱ ዘታይምስ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
በፈረንሳይ የተንቀሳቃሽ የነፍስ አድን /የአደጋ ደራሽ/ አገልግሎት ሰጪ መ/ቤት ሃላፊ ያን ፈለ እንደገለፁት “ካለፈው ፀደይ ወራት ጀምሮ በተራሮች አከባቢ የስደተኞች የነፍስ ማዳን ስራ የእለት ተእለት ተግባራቸው መሆኑ ገልፀው በክረምት ጊዜ የማቋረጥ ጉዞ እንደሚቀንስ ተስፋ እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡” ይህም እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት፡፡
ጉዞው የሚያደርጉት ስደተኞች ብዙ ችግሮችና አደጋዎች እንደሚያጋጥማቸው ይናገራሉ፡፡ እንደ ሚለ ገለፃ “ የሆነ አደጋ /መቅሰፍት/ እንደሚደርሳቸው ይገልፃሉ፡፡ የበረዶ ግግር ናዳ ወይም የስልካቻቸው መስመር አለመስራትና ትክክለኛ ቁጥር አለመታወቁ የሟቸች ደብዛቸው እንደሚጠፉ የደረሱበት የማይታወቅ እና አስከሬናቸው በፀደይ ወራት እንደሚገኝ” ይናገራሉ፡፡
ባፈው ወር ብቻ በጣልያን የባህር ጠረፍ በኩል ስደተኚች ለነፍስ አድን ሰራተኞች የድረሱልን ጥሪ ወደ 6 ጊዜ ማሰማቻቸውና መደወላቸው ይናገራሉ፡፡ በታህሳስ 20 ቀን 6 ስደተኞች ወደ ነባቼ ከተማ ሲያመሩ በተራሮች ውስጥ አቅጣጫቸው ስለጠፋባቸው የድረሱልን ጥሪ እንዳሰሙ ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳይ ቀን ሶስት ህፃናት ስደተኞች በተመሳሳይ ችግር እንደተገኙና አብዛኛዎቹም የአሰልጣኞች ልብስ የከባድ መኪና ሹፌሮች የስፖንዳ ልብስ ለብሰው መገኛታቸውና ለአስከፊው የበረዶና የቀዝቃዛማው አየር ሁኔታ የማይከላከል ልብስ መሆኑም ሰጋቱ የከፋ ያደርገዋል፡፡
ከ10 ቀን በፊት 12 የሚሆኑ የአፍሪቃ ስደተኞች በብዱን ሆነው ሲጓዙ ማዳን እንደተቻለና አንዳንዶቹ ጫማቸውና ጓቲያቸው በጎድጓዳው የበረዶ ጉድጓድ እንደተቀበሩ ይናገራሉ፡፡ የብዱኖቹ አባላት ለማዳን በማለዳ ገስገሰውና የ11 ኪሎ ሜትር ጉዞ ጀምረው ከ1,700 ሜትር በላይና ከሃይለኛው የበረዶ ግግር ግብግብ መግጠማቸውና ትግል መግጠማቸው ይናገራሉ፡፡
ለጉዞው የሚጠቀሙባቸው ሁለት ዋሻዎች ሲኖሩ የፈረንሳይ ፖሊሶች ግን ዋሻዎቹ ጫፍ አፋፍ ላይ ቆይተው እንደሚመልሳቸውና እነዚህ ህገ-ወጥ ስደተኞች ተይዘው በአውቶቢስ ባርዶንቺያ ወደ ተባለቸው ከተማ ወደ ጣልያን ወገን ያለው ዳርቻ እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡
የባርዴኔቺያ ከንቲባ የሆኑት ሚስተር ፍራንቼስኮ አቫቶ እንደሚሉት ከሆነ “ የአየር ሁኔታው ዋናው እንቅፋትና የችግር መንስኤ መሆኑ ይናገራሉ፡፡ በተለይም ህፃናት ለተራራው መውጫዎች አስፈላጊውን ትጥቅ ስለሌላቸው ለችግሩ አይነተኛ ቀማሽ /ገፊት ቀማሽ/ ሆነዋል፡፡ ህይወታቸውም ያጣሉ፡፡ በረሃውንና የሜዲትራንያን ባህርን አቋርጠው ሲያበቁ የመጨረሻዎች ማይል /ኪሎ ሜትር/ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ትሆንባቸውና በ15 ደቂቃዎች በማይሞሉ ጊዜያት በረሃብና በሙቀት ለሚነሳው በሽታ ይጋለጣሉ” ሲሉ ይገልፃሉ፡፡