ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች ስደተኞችን ከሊብያ እየመለሱ ነው
የፎቶ ምንጭ: AFP. በፈረንጆቹ ህዳር 20 – 2017፤ ከሊቢያ የተመለሱ የአይቮሪኮስት ስደተኞች በአቢጃን ኤርፖርት ሲደርሱ፡፡
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በሊቢያ ስደተኞች ለባርነት እየተሸጡ መሆኑን በሚዘገብበት በዚህ ወቅት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ አስወጥተው እየመለሱ ነው፡፡
በቅርቡ በፈረንጆቹ ህዳር 21 በናይጄርያ አቡጃ በተካሄደው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ECOWAS) ስብሰባ ላይ፤ ሰኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል መሄጃ አትተው የሚገኙትን የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞችን ወደሀገሮቻቸው ለመመለስ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቡርኪናፋሶ አምባሳደርዋን ከሊቢያ ያስወጣች ሲሆን በብዙ የአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ የሊቢያ ኤምባሲዎች ደጃፍ ላይ አስደንጋጭ በሆነው ስደተኞችን ለባርነት የመሸጥ ተግባርን በመኮነን የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡
በህዳር ሁለተኛው ሳምንት ላይ፤ 135 የቡርኪናፋሶ ዜጎች ድጋፍ ተደርጎላቸው በበጎፈቃደኝነት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተመቻቸላቸው ሲሆን፤ በህዳር ሶስተኛው ሳምንት ላይ በተደረገ ስደተኞችን ወደሀገራቸው የመመለስ ስራ ደግሞ 155 ስደተኞች ወደ አይቮሪኮስት ተመልሰዋል፡፡
ወደሀገራቸው የተመለሱት የአይቮሪኮስት ከስደተ ተመላሾች እንዳረጋገጡት ሊቢያ ውስጥ በእውነትም የባርያ ንግድ አለ፡፡ ከትሪፖሊ የተመለሰ ዲያብዝ ባባ የሚባል ስደተኛ “ሊብያ ውስጥ አፍሪካውያንን ይሸጣሉ፤ እዛ ሰዎችን ይሸጣሉ፡፡ የ 15-ዓመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊ ሊብያውያን እንኳ መኪናቸው ውስጥ ሆነው፣ ታጥቀው በመምጣት አፍነው ይወስዱህና፤ በ 200 ዲናር ወይም 100 ዲናር ይሸጡሃል፤ ሌሎች ደግሞ መልሰውይሸጡሃል፤ እውነታው ይህ ነው፡፡” ብሏል፡፡
በሁለት በረራዎች ተጭነው የተመለሱ ብዙ ወጣት የቡርኪናፋሶ ሰደተኞች ለ IOM ሰራተኞች እንደተናገሩት፤ ቀደም ሲል ከሊብያ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ፍላጎቱ ነበራቸው፡፡
“አውሮፓ ለመድረስ እፈልግ ነበር እንዲሁም ደግሞ ቤተሰቦቼን ከድህነት ለማውጣት የሆነ ገቢ ለማግኘት ተስፋ ነበረኝ፡፡ በኒጀር የሚገኘውን የአጋዴዝ በረሃ አቋርጬ ሊቢያ ገባሁ፡፡ ሊቢያ ውስጥ ስምንት ወራት ቆየሁ፤ በእስር የቆየሁባቸውን ሰባት ወራት ጨምሮ፡፡ እጅግ በጣም ያስፈራል” ይላል ከነዚህ ወጣት ተመላሾች አንዱ የሆነው ዴምበል ሙስጠፋ፡፡
“አሁን ሂወትን እንደአዲስ ቡርኪናፋሶ ውስጥ እንድጀምር ለተደረገልኝ እገዛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ሻንጣ ሳልይዝ ነው የመጣሁት ብዙ ብርም ጠፍቶብኛል” ሲል ጨምሯል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ