ጣልያን ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ልትቆጣጠርና ልታባርር ነው

አዲሱ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስተር በአገራቸው ያሉ ስደተኞች አቀባበል የነበሩ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ እንዲቀየሩ እየጠየቁ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆንቲሎኒ ከእሳቸው በፊት ሚኒስተር የነበረ ማተዮሬ የሚከተለውን አገባብ በተለየ ትኩረት በመከታተል ለሕገ-ወጥ ስደት እንደሚታለው ቃል ገብተዋል፡፡ ከጆንቲሎኒ ጥሪ ጋ ተያይዞ፤ የኢጣልያ ሲቪላዊ ድህንነት ሃላፊ ፍራንኮ ጋብሪየሊ “እያደገ የመጣ የስደተኞች ተፅእኖ መረጋጋትና ይሉኝታል የሰፈነባት አህጉራዊ ሁኔታን “ለመታገል ያለመ ሰነድ አዛጋጅተዋል፡፡

በአዲስ አመታችን ዋዜማ በሁሎም የጣልያን ጣብያዎች የተሰራጨ ባለ ሁለት/2/ ገፅ መመርያ፤ ፖሊስ የተለየ እርምጃ በመውሰድ ለሕገ-ወጥ ስደተኞች ሊቆጣጠራቸውና ከአገሩ ሊያባርራቸው የሚያዝዝ ነው፡፡

ይህ መግለጫ በልደት በአል በበርሊን ጥቃት የፈፀመ አሸባሪ በሚላኖ ከተማ ከተገደለበት ሳምንት በፊት የወጣ ነው፡፡ለዚህ ጥቃት የፈፀመ ቱኒዝያዊ ስደተኛ አኒስአልዓምሪ በ 2011 ወደ ኢጣልያ ሲገባ፤ በ 2015 ከውህነ ቤት በመሳናበት ከአገሪቱ እንዲወጣ በፍርድ ቤት ውሳነ ተሰጥተዋል፡፡ ይህ በበርሊን ከባድ የጭነት መኪና ሽፌር ተኩሶ በመግደል ያደረሰው አደጋ አንዲት /1/ ጣልያናዊት ጨምሮ የ 12 ሰዎች ህይወት አጥፍተዋል።

ከ 2014 ጀምሮ እስከ ዛሬ ከግማሽ ሚልዮን ስደተኞች ወደ ኢጣልያ ገብተዋል፡፡ በመጀመርያ 2016 በመካከለኛው ባህር ወደ ኣውሮፓ የሚስገባ መንገድ ከተዘጋ በሃላ፤ የኢጣልያ ባህር ዳርቻ የረገጡ የስደተኞች ቁጥር ከ አምስት/5/ እጅ በላይ ጨምረዋል፡፡

እንደ የተባበሩት አገሮች ድርጅት የበላይ ተወካይ አገላለፅ፤- በ 2016 ከ 180000 ስደተኞች በላይ ከሰሜን አፍሪካ ዳርቻ/ድንበር/ ተነስተው ወደ ኢጣልያ ገብተዋል፡፡

በ2015 በዚህ አመት 270000 የሚያህሉ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ከአገሪቱ ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ተሰጥተዋል። በፓሪስ በሚገኘው የመረጃ ምግባረ ሰናይ ዶብ አልባ የሃኪሞች ማህበር አገላለፅ፡ የኢጣልያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ስደተኞች ከአገራቸው ከመባረራቸው በፊት የሚታጎርበት አዳዲስ የማቆያ ማእከሎች እንዲከፍት ፕሮግራም ይዘዋል፡፡