ቤልጂየም ሱዳናውያን ስደተኞችን ወደሀገራቸው ልትመልስ ነው

ብራስለስ የሚገኘው የማክሲሚልያን አደባባይ ስደተኞች ሰፍረውበታል፡፡ የፎቶ መንጭ: www.xpats.com

የቤልጂየም የጥገኝነትና የስደተኞች ጉዳይ ሚኒስትር በአሁኑ ወቅት ብራስለስ በሚገኘው የማክሲሚልያን አደባባይ ላይ ሰፍረው የሚገኙ ህገወጥ ሱዳናውያን ስደተኞችን ወደሀገራቸው ለመመለስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ዕቅድ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትር ቲዎ ፍራንከን እንዳሉት፤ ሱዳን ለስደተኞቹ የጉዞ ሰነዶችን ለመስጠትና መልሳ በሀገራቸው ለመቀበል ዝግጁ ነች፡፡ ብራስለስ የሚገኘው የሱዳን ኢምባሲ የራሱን ዜጎች ለመለየትና ወደ ሱዳን ይመለሱ ዘንድ አስፈላጊ የሆኑትን የጉዞ ሰነዶች ለማሰናዳት አንድ ቡድን ወደ ማክሲሚልያን አደባባይ ይልካል፡፡
ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፤ አብዛኞቹ ከኤርትራና ከሱዳን የመጡ እስከ 600 የሚደርሱ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት አደባባዩ ላይ ሰፍረዋል፡፡

የቤልጂየም ፖሊስ በአገሪቱ የሚገኙ ህገወጥ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይቀጥላል ብለዋል ቲዎ ፍራንከን፡፡ የስደተኞች ጉዳይ ሰራተኞች የጥረዛውን ሂደት ከመጀመራቸው በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉት ስደተኞች ቤልጂየም ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት ማመልከቻ የማቅረብ መብት አላቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
ሱዳን ከአፍሪካ ቀንድ ለሚሰደዱ ህገወጥ ስደተኞች መነሻና መተላለፍያ ሀገር ነች፡፡ ሀገሪቷ ህገወጥ ስደትን ለመዋጋት ከአውሮፓ ህብረት ጋር በትብብር እየሰራች ሲሆን፤ ከቀጠናው ወደ አውሮፓ የሚደረግ ስደትን ለመግታት ከአውሮፓ ህብረት የኢመርጀንሲ ትረስት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ ይደረገላታል፡፡