የሊቢያ ባህር ወደብ ጠባቂዎች የ11 ስደተኞችን አካል ሰብስበዋል
የሊቢያ ባህር ወደብ ጠባቂዎች ከሳብራታ ከተማ ከትሪፖሊ በምእራብ በኩል 70 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኘው የሊብያ ወደብ በኩል ወደ ጣሊያን ለማቋረጥ ሲሞከሩ ህይወታቸው ያለፈን የ11 ስደተኞች አካል በሚያዝያ 22 መሰብሰባቸውን ገልፃል፡፡
የባህር ወደብ ፓትሮል 2 ጀልባዎች 11 ህገወጥ ስደተኞች አካል ሬሳ በመሰብሰብ ሌሎች 83 በፕላስቲክ ጀልባ ላይ ከሰብራታ ወደብ 5 ማይል ርቆ ሰብሰበዋል፡፡ የሊቢያ ወደብ ጠባቂዎች ቃል አቀባይ ጄኔራል አዩብ ቃስም ለዚኖዋ እንደገለፁት ጀልባው ፓትሮሉ ሲደርስ ተሰብሮ ነበር፡፡
2ኛው ጀልባ ዝሊቴን 135ኪሜ/84 ማይል ከምስራቅ ትሪፖሊ 200 ስደተኞችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ 38 ሴቶች እና 1 ህፃን፣ ከፓኪስታን፣ ባንግላዲሽ እና ህንድ የመጡ ይዞ ሲጓዝ እንዲቆም ተደርጓል፡፡
ካለፈው ሐምሌ ጀምሮ ከማእከላዊ ሜድትራንያን ባህር ማቋረጥ የሊቢያ ባለስልጣናት በጣሊያን እገዛ የአገር ውስጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር ባደረጉት ጥረት እና በሊቢያ የባህር ጠባቂዎች ጀልባዎችን መጠበቅ በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል፡፡
በሚያዝያ 10ኛው ተከታታይ ወር የሊቢያ ባህር ወደብ ጠባቂዎች የሰው አዘዋዋሪ ጀልባዎችን ስጋት ባለው መልኩ ወደ አውሮፓ ሲያቋርጡ ጣልቃ በመግባታቸው ሊቀንስ ችሏል፡፡
የጣሊያን ኔቪ እና የባህር ወደብ ጠባቂዎች የሊቢያ ኔቪ እና ባህር ወደብ ጠባቂዎች፣ የአውሮፓ ህብረት ተልኮ ኢዩናቭ4 እና መያሎች በአደገኛ ባህር በፕላስቲክ ጀልባ ሊያቋርጡ ቢሞክሩም ስደተኞችን ማዳን ላይ በንቃት ይሰራሉ፡፡ በርካታ የተገኙ ስደተኞች ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል፤ ወደ ሃገራቸው እስኪመለሱ እንዲቆዩ ተደርጓለል፡፡
በዚህ አመት የመጀመሪያ 3 ወር ውስት 3,479 ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ህፃናት ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል፡፡
በሚያዝያ 3ኛ ሳምንት በአይኦኤም ሪፖርት መሰረት 5,775 ስደተኞች ከሊቢያ 23/4/2010 ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓለል፡፡ ባለፉት 5 ወራትም ከ12,000 በላይ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ ከ2009 መጀመሪያ ጀምሮ አይኦኤም ባጠቃላይ ወደ 25,145 ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ከ30 የተለያዩ ሀገራት እንዲመለሱ አድርጓል፡፡
ፎቶ ክሬዲት ሲ.ፒኢቲአርኢ/አይኦኤም አንዱ ልጅ ትሪፖሊ ማቆያ ማእከል
TMP – 19/05/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ