ኢትዮጵያ ስደተኞችን እና ማህበረሰቡን ለመደገፍ ስትራቴጂ ተገበረች

ኢትዮጵያ የ10 አመት አጠቃላይ የስደተኞች ምላሽ ስትራቴጂ ትግበራ ላይ መሻሻል እያሳየች ሲሆን ስደተኞችን እንደሚጠቅም እና ለተቀባዩ ማህበረሰብ በጎ ተጽእኖን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፤
የኢትዮጵያ አጠቃላይ የስደተኞች አቀባበል ፍሬም ወርክ/ ሲአርአርኤፍ/ የተቀረጸው ሀገሪቱ እ.ኤ.አ በመስከረም 2016 የኑዮርክን የጥገኞች እና ስደተኞች ስምምነት ስታደርግ 9 ተግባራትን ለማከናወን የገባችውን ቃል እውን ያደርጋል በማለት ነው። ፍሬም ወርኩ ስደተኞችን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመጥቀም ልማትና የበጎ አድራጎት እርዳታ በአንድነት በመቀላቀል ለ ዘላቂ መፍትሔ ይጥራል፡፡
አፍሪካ ውስጥ እንደ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የስደተኞች ተቀባይ ሀገር መጠን, ኢትዮጵያ በ 6 ክልሎች ውስጥ ባሉ 27 የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ከ900,000 በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች፡፡ የስደተኞቹ 3/4ኛ ከደቡብ ሱዳን፣ እና ሱማሊያ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ከኤርትራ፣ ሱዳን እና 15 ሌሎች አገሮች የመጡ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ 20/9/2016 በ ኒውዬርክ በተደረገው የመሪዎች የስደተኞች ሰሚት ነበር ስደተኞችን ለመጥቀም 9ኙን ቃልኪዳን የተቀበለችው፡፡
የስደተኞችን ማህበራዊ ቅንጅት መልካም አጋጣሚ ለመፍጠር እነዚህ ስምምነቶች ከካምፕ ውጪ የመስፋፋት ፖሊሲ፣ የስራ ፍቃዶች መስጠት፣ በሁሉም የትምህርት ደረጃ የስደተኞችን ተሳትፎ ከፍ ማድረግ፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች ለስደተኞች ማበልፀግ፣ የስተደኞች የሲቪል ምዝገባ፣ የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ፣ የመንጃ ፍቃድ እንዲያወጡ፣ ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ ላላቸው የውጭ ዜጎች ያሉ ሌሎች ሁሉንም ጥቅማ ጥቅሞች እንዲያገኙ ማድረግ ናቸው፡፡
ስደተኞችን አያያዝ የተከለሰ ረቂቅ ህግ ከፀደቀ በኋላ 9ኙም በሙሉ ህግጋት ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚነት እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር /ኤአርአርኤ/ ምክትል ዳይሬክተር እንደገለፀጹ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል አቶ ጀማል ዘይኑ አሳውቀዋል፡፡
የስደተኞች የሲቪል ምዝገባ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ጨምሮ በጥቅምት 2017 እ.ኤ.አ በአገሪቱ ባለፉት 10 አመታት የተወለዱ በግምት 70,000 ስደተኛ ልጆች የምዝገባ መብት ለመስጠት አስችሏል፡፡
የባዮሜትሪክ መረጃ አስተዳደር ሲስተም በ2017 እ.ኤ.አ. በአገሪቱ ዙሪያ ያሉ ስደተኞች ላይ መሰረታዊ መረጃ ሪኮርድ ለማድረግ ተጀምሯል፡፡ የባዮሜትሪክ ሲስተሙ እና የሲቪል ምዝገባ አጠቃላይ የስደተኞች ምላሽ ፍሬም ወርክ /ሲአርአርኤፍ/ መልካም አጋጣሚዎችን ሰጥቷል፡፡
ከአውሮፓ ህብረት፣ እንግሊዝ እና ሌሎች ምንጮች በሚገኝ ፈንድ ኢትዮጵያ የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ከፍ ለማድረግ እና ስደተኞች እንዲቀናጁ ለማገዝ ዋጋው 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የኢንዱስትሪ ፓርክ እየገነባች ነው፡፡ ፓርኮቹ እስከ 100,000 ያህል ስራዎች እንደሚፈጥሩ የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 30 በመቶ ለስደተኞች የሚያዝ ይሆናል፡፡
ቢያንስ 10,000 ሄክታር በመስኖ ሊያዝ የሚችል መሬት የሚቀርብ ሲሆን 20,000 ስደተኞች እና የአካባቢው ህብረተሰቦች ግብርና ላይ እንዲሰሩ ያስችላል፡፡ የግብርና ፕሮጀክቶች በአገር ውስጥ ከ20 አመት ወይም ከዚያ በላይ ለኖሩ ስደተኞች መቀናጀት የሚያስችል ሲሆን 1,000 ሄክታር መሬትም ሶማሌ ክልል ላሉ ስደተኞች ተሰጥቶ 411 ስደተኞች ግብርና ላይ እንዲሰሩ አስችሏል፡፡
ጆን ማጎግ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ አንዱን የብሔራዊ ምክክር የተሳተፈ የሲአርአርኤፍ ሞዴሎች ትግበራን ሲገልፅ ፍሬም ወርኩ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸውን አያያዝ ሁኔታ ወደ ተገቢ ለውጥ በማሸጋገር ለህይወታቸው መልካም አጋጣሚዎችን ይፈጥራል፡፡ አዲስ ህይወት መጀመር ይችላሉ፡፡ ይህም የደህንነት፣ ተቀባይነት እና የህይወት ተስፋ ስሜትን ይሰጣቸዋል ብሏል፡፡