ኦስትሪያ ሞባይል ስልኮችን እና ጥሬ ገንዘብ ከስደተኞች ለመውረስ ውጥን ይዛለች
በሚያዝያ 18 የኦስትሪያ ካቢኔት ባለስልጣናት የጥገኝነት ጥያቄዎችን ስልክ እና ጥሬ ገንዘብ እስከ ዩሮ 840 እንዲወርሱ እና ውድቅ የተደረጉ ጥገኝነት ጠያቂዎች አገሪቱ ውስጥ መቆየት አስቸጋሪ እንዲሆንባቸው አፅድቀዋል፡፡
ቻንስለር ሰባስቲያን ኩርስ ለዜና ምንጮች እንደገለፁት “እራሳችንን በሚገባው አውቀን ህገወጥ ስደተኝነትን ለመዋጋት እና ጥገኝነትን አላግባብ መጠቀምን ለማስቀረት ቆመናል” ብለዋል፡፡
ጥገኝነት ጠያቂዎች ማንነታቸውን ለመለየት፣ የወንጀል ታሪክ እና የምድራዊውን አቀማመጥ የመረጃ ትንታኔ ለማግኘትና ኦስትሪያ ከመድረሳቸው በፊት የተጓዙበትንና ያለፉበትን መስመር ለመለየት ሞባይል ስልካቸውን እንዲያስረክቡ ይጠየቃሉ፡፡
አመልካቾች ከዚህ በፊት የአውሮፓ ህብረት አገር ገብተው ከሆነ ወደዚያው እንዲመለሱ ይደረጋል፤ ምክንያቱም በዱብሊን ደንብ መሰረት ስደተኞች ጥገኝነት ሊያመለክቱ የሚችሉት መጀመሪያ የገቡበት የአውሮፓ ህብረት አገር ነው፡፡ ከስልኮች ላይ የሚሰበሰብ መረጃ ስደተኞች ማንኛውም ወንጀል ስለመስራታቸው ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
ጥገኝነት ጠያቂዎች በህግ ለባለስልጣናት እንዲያስክቡ የሚጠበቅባቸው ገንዘብ ለማመልከቻ ሂደታቸው፣ ለምግብ እና መኖሪያ መሸፈኛ ይውላል፡፡
በተወጠነው ሰነድ የተያዙ ሌሎች እርምጃዎች የጥገኝነት ጠያቂዎች ወንጀል የፈፀሙ ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ባይደርሱም በፍጥነት ከአገር እንዲወጡ ማድረግ ያካትታል፤ ሰነዱ በተጨማሪ ወንጀለኞች ወደ ማቆያ ማእከሎች የእስራት ጊዚያቸውን ከጨረሱ በኋላ ከአገር እንዲወጡ ለማድረግ እንዲጠብቁ ይገልፃል፡፡
ሰነዱ ዶክተሮች እና ሆስፒታሎች ለባለስልጣናት ጥገኝነት ጠያቂዎች ህክምና ሲያስፈልጋቸው እንዲያሳውቁ ማለትም የተሻለ ስኬታማ የአገር ማስወጣት ዝግጅት እና ትግበራ ለማረጋገጥ ማሳወቅ እንዳለባቸው ያረጋግጣል፡፡
የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ኸርበርት ኪክል የቀኝ ክንፍ ፖፕሊስት ነፃ ፓርቲ ኦስትሪያ እንደገለፁት የሰነዱ አላማ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ ገዳቢ እና ተፈፃሚ ህግ እንዲኖር ማድረግ ሲሆን እንደእሳቸው ጥብቅ እና ቀልጣፋ ህግ አውስትራሊያ ውስጥ የጥገኝነት መብት ጥሰት ለመከላከል ያስችላል፡፡
ውድቅ ለተደረጉ ጥገኝነት ጠያቂዎች እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን ባለ አዲስ ህግ መሰረት ከአገር መውጣት የሚጠብቁ ካላቸው ዲስትሪክት እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም፡፡
ጥገኝነት የተሰጣቸው በትንሹ ለአስር አመት መጠበቅ እና ማለትም ከ6 አመት ጥበቃ ይልቅ ለዜግነት ከማመልከታቸው በፊት መቆየት ይኖርባቸዋል፡፡
አዲሱ ህግ እንደገዳቢ በመሆን የስደተኞችን ገንዘብ ስናረጋገጥ በርካቶች ወደዚህ ላለመምጣት ሊወስኑ ይችላሉ እንደ ምክትል ቻንስለር ሄንስ ክርስቲያን ስታርቺ፡፡ ሰነዱ አሁኑ በፓርላመንት መጽደቅ ይኖርበታል፡፡
የኦስትሪያ ባህል በአዲስ መጤዎች በከፍተኛ ደረጃ ተጽእኖ ስለሚያድርበት ለስደተኞች ያለው የመጀመሪያ ርህራሄ ተለውጧል፡፡ በ2007 የስደተኞች ቀውስ አስከትሎ ኦስትሪያ 150ሺ የጥገኝነት ማመልከቻዎች ተቀብላለች፡፡ ይህ ያላት ህግ 8.7ሚሊዮን አኳያ 1.7 በመቶ ነው፡፡
መንግስት መቀናጀት በጀት በከፍተኛ ደረጃ ቆርጧል፡፡ በሚያዝያ መጀሪያ ባለው እቅድ እንደተገለፀው መዋእለ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆችን የራስ እስካርቭ እንዳይጠቀሙ ለማድረግ ተወስኗል፡፡ ባለፈው አመት የአውስትሪያ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ ትምህርት ቤት እና ህዝባዊ ቦታዎች ሙሉ ፊት ሽፋን ከልክሏል፡፡ ቀደም ብሎ ሚ/ር ኪክል የአውሮፓ ህብረት ባልደረቦችን የማንም የጥገኝነት ማመልከቻ አውሮፓ ውስጥ የሚፈፀም እንዳይፈቅዱ ግፊት እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ይልቅ ከአውሮፓ ውጪ ለጥገኝነት አመልካቾች በትራንዚት ዞኖች ውስጥ እንዲያመለክቱ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡
ስደተኛ ኢንስብሩክ፣ ኦስትሪያ ውስጥ በ21/2/2008 ዓ.ም መንገድ ላይ ሲለምን የሚያሳይ ፎቶ
TMP – 18/05/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ