በሊብያ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ እየተደረገ ያለ የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ እርዳታ!

The Mixed Migration Working Group (MMWG) የተባለ በስደተኞች ዙርያ የሚሰራ ተቋም እንደዘገበው ከትሪፖሊ በ 115 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኝ ዝዋራ ተብላ በምትጠራ የመንግስት የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ያሉበት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ መጥተዋል።

ይህ The Mixed Migration Working Group (MMWG) ተብሎ የሚጠራ ተቋም ከየተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮምሽን (UNHCR)፣ ከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ (UN refugee agency) እንዲሁም ከዐለም ዐቀፍ የህክምና ቡድን (International Medical Corp)፣ ዳኒሽ የስደቶች ጉባኤ (Danish Refugee Council)፣ ኣይኦኤ(IOM) እና ሌሎች የተውጣጣ ግብረ ሀይል ነው። ይሄ ግብረ ሀይል በየተባበሩትመንግስታት የሰብኣዊ መብት ኮምሽን (UNHCR) ተባባሪ መሪነት እየትነቀሳቀሰ ሊብያ ላይ ያለ የስደቶች ህይወት ለመታደግ የሚተጋ ነው።

እስከ ሚያዝያ 18 እ.ኤ.አ 800 የሚደርሱ የአፍሪካ እና የደቡብ ኤሽያ ሀገራት ስደተኞች ከሰው በላ የሰው ዝውውር ወረበላዎች ሲድኑ የዚህ ግበረ ሀይል እርድታ ከፍተኛ ነበር። በዚህ ግበረ ሀይል አማካኝነት በተሰሩ መጠለያ ቦታዎች እንዲጠለሉ ተደርገው ነው ከሞት የዳኑት። ለዚህ የህይወት መታደግ ስራ የሊብያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም የበኩላቸው ተወጥተዋል።

እነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ የመጡት ከካሜሮን፣ ባንግላድሽ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምብያ፣ ጋና፣ ጉያና፣ ኢቨሪኮስት፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄርያ፣ ፓኪስታን፣ ሰኔጋል፣ ሶማልያ እና ሱዳን ሲሆኑ ወደዚህ መጠልያ ከመምጣታቸው በፊት ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ እጥረት ባለበት ቦታ ለሳምንታት ታግተው የቆዩ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ውድቀትም አጋጥሞዋቸዋል።

የግብረ ሀይሉ አባላት( MMWG) ስድተኞቹ ከነበሩበት መዐት አውጥተው ወደ ስድተኞች ካምፕ እንዲገቡ በማድረግ ሰብአዊ እርዳታዎችን ሲሰጣቸው ቆይተዋል። ይህ እርዳታ ከሀገሪቱ አከባብያዊ መስተዳድር አካላት በጋራ በመሆን የተደረገ ነው። ታግተው በነበሩበት ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ጉዳት የደረሰባቸው ስደተኞች በአየር ወደ ትሪፖሊ እንዲጓዙ ተደርጓል። ይህ የሚደረገው ወደ ባህር ዳርቻው መውጣት የምያስችል ሰለማዊ የፀጥታ ሁኔታ ሊብያ ላይ ስሌለ መሆኑን ተገልፀዋል።

Médecins Sans Frontières (MSF) የተባለ ድርጅት እና የግብረ ሀይሉ አባላት (MMWG) በጋራ በመሆን የመድሀኒት እና የምግብ አቅርቦት በመርዳት መልካም ስራ እየሰሩ ነው። ከስድተኞቹ ቁጥር መብዛት እና የምግበ-ውሃ ማነስ ምክንያት አሁን እየተደረገ ያለ እርዳታ ከፈተኛ ጉዳት ላለባቸው ብቻ መሆኑም ተብራርተዋል።

በሚያዝያ ወር መጀመርያ አይኦኤም ያዘጋጀው አንድ ፕሮግራም ነበር። ሊብያ ላይ ካሉ የካሜሮን፣ ጉያና፣ ኤቪሪኮስት፣ ማሊ፣ ናይጄርያ እና ሴኔጋል ኤምባሲዎች የተውጣጣ ቡድን የስደተኞች ካምፑን እንዲጎበኙት ተደርጓል። በመሆኑም እነዚህ ሀገራት 355 ስደተኞች ወደየሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ ስራ መጀመራቸው ተገልፀዋል። ሌሎች 186 ስደተኞችም በየሀገራቱ ውስጥ ተመዝግበው ተይዘዋል። እነዚህ ከሊብያ የሚመለሱ ግን ከዝዋራ-ሊብያ የሚነሱበት ቀን በግንቦት መጀመርያ ወር ላይ እንደሚሆን ተገልፀዋል።

ከእነዚህ 800 ሊብያ ላይ የነበሩ ስደተኞች 88ቱ ከፍተኛ ችግር የደረሰባቸው ሆኖ ወደ ትሪፖሊ ሄደዋል። የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ኮምሽን እንደሚለው እንደዚህ ዐይነት ከፍተኛ ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ወጥተው ይታከማሉ።

ይህ የፈረንጆች ዐመት ከተጀመረ ወዲህ በድምር 5109 በሊብያ ባህር አደጋ ላይ ወድቀው የነበሩት ስደተኞች በሀገሪቱ የባሀር ሀይል አባላት ህይወታቸው ከሞት ተርፈዋል። እነዚህ ስደተኞች ብዙ ስደተኛ ወደየሌላቸው የሀገሪቱ የስደተኞች ካምፕ ይመደባሉ።

ፎቶ: IOM. በአቡ ሳሊም የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የምትገኝ ሴት ጊዜዋን ስእሎችን በመሳል ስታሳልፍ ያሳያል

TMP – 06/06/2018