የሱዳን ባለስልጣኖች 136 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው አባረሩ

56 ህፃናትና 16 ሴቶች የሚገኙባቸው  136 የኤርትራ  ስደተኞች  ከሱዳን   ወደ  ትውልድ  ሃገራቸው  ኤርትራ  በመጀመርያው  የሚያዝያ  ሳምንት  እንዲመለሱ እንዳደረገ  የኤሪ-መድረክ  ሬድዮ አስታወቀ ፡፡

ዘገባዎች  እንደሚያመለክቱት   ወደ ትውልድ  ሃገራቸው  የተባረሩት የኤርትራ  ዜጎች  ከ180  የሊቢያና  የኤርትራ  ስደተኛት  በሱዳን  የፀጥታና  ድህንነት  ሃይሎች  በቁጥጥር  ስር ከዋሉት  መካከል ናችው፡፡  የስደተኞቹ  ቡድን  በህገ-ወጥ  የሰው አዘዋዋሪዎች  በኮንቴይነር  ታሽገው  በፖርት  ሱዳን  ወደ ውጭ አገር  ለመሄድ  በመጠባበቅ ላይ  የነበሩ  ናቸው፡፡

ሱዳን  የድንበር ቁጥጥርሯ  ባጠበቀችበት  በኣሁኑ  ወቅት  በርካታ   የፀጥታና  የደህንነት ሃይሎች  ያሳማራቸው  በቅርቡ  በ2014  የፀረ  ህገ-ወጥ የሰው  አዘዋዋሪዎች  ህግ በማፅደቅና  በዚህ  ህገወጥ  ስራ   ተሰማርተው   የተገኙ  ማንኛውም  ዜጋ  እስከ 20  ዓመት  ፅኑ እስራት  እንደሚቀጣ  ታውቀዋል ፡፡

የሱዳንና  የኤርትራ  ባለስልጣናት  ኤርትራውያን  አገራቸው  ለቀው  እንዳይወጡ  በትብብር  እየሰሩ   ነው፡፡ እንደኣፍሪቃ ሞኒተር  ዘገባ  ከሆነ  ሁለቱም  አገሮች  የሱዳን  ባለስልጣናት  ከኤርትራውያን  ስደተኛች   አገራቸውን  ጥለው   ድንበር  አቋርጠው  እንዳይሄዱ  የሚያግድና  ከተያዙም   ወደ ኤርትራ   መንግስት  እንዲያስረክቡ  የሚስችል  ስምምነት   አድርጓል ፡፡ የአፍሪካ  ሞኒተርስ  ዘገባ  እንደሚያሳይ  ከሆነ  ከ2016 አጋማሽ   ጀምሮ  የህገወጥ ስደተኛች  ኤርትራውያን  ከሱዳን  የሚባረሩት  ቁጥር  እያሸቀበ  መሆኑ  ነው፡፡

ከአመቱ  መጀመርያ  ጀምሮ  የሱዳንና  የኤርትራ  የድህንነት   ሃይሎች  በካርቱምና  በከሰላ  የሚገኙ  የህገ-ወጥ  ሰው አዘዋዋሪዋች  መርበብ  ለመበጣጠስ  እየሰሩ  መሄኑ  ታውቀዋል፡፡