ከቤተ ሰብ ጋር የመገናኘት ስራ በጀርመን ለሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ፈታኝ ሆነዋል።

በጀርመንይ የሚኖሩ ኤርትራውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት በጣም እንደተቸገሩ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፤ ዶቸቬለ ገለፀ። ፈታኝ የሆነበት ምክንያትም ኤርትራ በሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ የቪዛ እጥረት ስለገጠመው እና በየ ጎረቤት ሀገራቱ እየሄዱ ማስፈፀም ረጅም ጊዜ የሚወስድ ስርዐት ስላለው መሆኑ ተገልፀዋል።

ጀርመን የሚገኙ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያዌአቸው ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት ከቤተ ሰብ ጋር አብሮ ስለመኖር የሚያመልክት ጥያቄ ማቅረብ አለባቸው። ኤርትራ ያሉ የቤተ ሰቡ አባላትም እንደዚሁ ይሄንን ጥያቄ በሶስት ወር ውስጥ ማመልከቻቸውን ወደ ጀርመን ኤምባሲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አሁን ግን ጀርመን ላይ ያሉ የኤርትራ ስደተኞች ይህ የቤተ ሰብ ጉዳይ ለማስፈፀም ወደ ጎረቤት ሀገራት መሄድ ግድ ይላቸዋል።

ወደ ጎረቤት ሀገር ሂደው ይህ የቪዛ ጉዳይ ለማስፈፀም የኤምባሲው አካላት ቀጥረው ለማናገር እስከ ሶስት ወር ጊዜ ይፈጅባቸዋል። ይህም ሆኖ ወሳኙ የኤምባሲው አካል ነው። ሊሳካም ላይሳካመ ይችላል።

ባለፈው አመት ብቻ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሱዳን የሚገኙ የጀርመን ኤምባሲዎች የ808 የኤርትራውያን ቤተ ሰብ ጉዳይ አስፈፅመዋል። ከእነዚህ ባለ ጉዳዮች 394 ማለትም 48.8% ብቻ ተቀባይነት አግኝተዋል።

የጀርመን ፓርላማ አባል ኡላ ጀልፔክ ለዶችቬለ እንደገለፁት የችግሩ ምንጭ “ከፍተኛ የቢሮክራሲ እከል” ነው ብለውታል።

በጀርመን የግራ ዘመም ፓርቲ የውስጥ ጉዳዮች ቃል አቀባይ እንዳሉት “ስደተኞች ከቤተሰቦቻቸው የማገናኘቱ ጉዳይ ይሄን ያክል ከባድ መሆኑ ያስደንግጣል። ይህ ለሰዎች ሰቆቋአዊ ህይወት ምክንያት ነው።” ብለውታል።

ፓርቲው እንዳለው ኤርትራውያን ስደተኞች የቤተሰቦቻቸው ቪዛ ለማስፈፀም የግድ የኤርትራ መንግስት ፓስፖርት እና ጥንዶች ደግሞ ህጋዊ ባለትዳሮች መሆናቸው የምያሳይ ህጋዊ ሰነድ ያስፈልጋችዋል የሚል ቅድመ ሁኔታ ምክንያታዊ አለመሆኑ ገልፀዋል።

ጀልፔክ እንዳሉት “ አንድ ፌደራላዊ መንግስት (ጀርመንን ማታቸው ነው) ከአንድ ወተሃደራዊ አምባገነን መንግስት ህጋዊ ሰነዶችን መቀበልን መታሰብ አልነበረበትም። በተፈጥሮ ሰዎች ወደ አምባገነን መንግስት መሄድ ይፈራሉ።” ብለዋል።

የፌደራል መንግስት ግን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎቹ ምክንያታዊያን ናቸው ብሎ ያምናል። በግራ ዘመም ፓርቲ ለተሰጠው አስተያየት “አምገነን መንግስት መሆን እና ኤምባሲዎች ላይ ፓስፓርት መከልከል ወይም ማዘገየት የምያገናኝ ነገር የላቸውም” ብለዋል።

ይህ መልስ ግን የቪዛ ማስፈፀም ሂደት በአማካይ ስንት ጊዜ መፍጀት እንዳለበት ሳይገልፅ ቀርተዋል።

“እንደማየው እና በተመኩሮ እንደማውቀው የቪዛ ስራ ለማስፈፀም እስከ ሶስት ወር የሚቆዩ አሉ። ዓመታትም ሊቆይ ይችላል። “ ብለዋል ጃልፔክ።

ሌላ ችግር ተብሎ የተጠቀሰ ጉዳይ የመጀመርያ አመልካቾች ቀጠሮአቸውን ስድስት ወር ካለፈው ይሰረዛል። በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ ከፍተኛ የሆነ የቀጠሮ ማነስ ችግር እንዳለም ተቀምጠዋል። ብዙ ኤርትራውያን የቤተ ሰብ ቪዛ ገዳይ የምያስፈፅሙበት አዲስ አበባ ነው።

አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ እና የቪዛ ጉዳያቸው ለማስፈፀም ወደ ኤምባሲው ሲሄዱ ከሚጠበቅባቸው አንዱ በአካል ተገኝተው ስማቸው ከማመልካቻው ጋር ማያያዝ ነው። ኤምባሲው አመልካቾቹን በየአመጣጣቸው ነው የምያስተናግዳቸው።

እንደ ጃልፔክ አባባል ከሆነ ከ20 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች አዲሰ አበባ በሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ጉዳያቸው እያስፈፀሙ ይገኛሉ፤ ለቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለሁም አመልካቾች። ዘገባው የዴቸቬለ ነው።

ፎቶ: ጀርመናውያን በጎ ፈቃደኞች በስደተኞች ካምፕ ዙርያ የልማት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ፤ ስቻርሁሰን፡ ጀርመን 26 ግንቦት 2016

TMP – 11/06/2018