ጠረፍ ጠባቂዎች ስደተኞችን ነፃ ለመልቀቅ ጉቦ ሲቀበሉ

ፎቶው የመዘገበ፡ ሂዩማኒቴሪያን ፕራክቲስ ኔትዎርክ 2016፡፡ ስደተኞች በሊቢያ ማቆያ ማእከል

የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እየታገዙ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩት ሰዎችን በማሰርና ጉቦ በመቀበል ሕገ-ወጥ የሆነ የሰዎች ዝውውር በማራመድ ላይ መሆናቸው ከሂዩማን ራይትስ ዎች የሚወጡት አዳዲስ ሪፖርቶች እያጋለጡ ነው፡፡
ጠረፍ ጠባቂዎቹ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ጀልባዎች ጉዞአቸውን በማቋረጥ ስደተኞቹ ለመፈታት ከፈለጉ ጉቦ እንዲከፍሉ በዘዴ በማታለል ገንዘብ እንደሚወስዱባቸው ከሂዩማን ራይትስ ዎች የተሰበሰቡት ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች ወደ አውሮፓ የሚገቡት ስደተኞችን ለመግታት የሚያደርገው ያለው ጥረት ከፍተኛ ሚና እያደረገ ነው፣ ለዚሁም የአውሮፓ ኅብረት ለጠረፍ ጠባቂዎቹ ተገቢው ሥልጠና በመስጠት ይተባበራል፡፡
አንድ ዕድሜው 30 ዓመት የሆነ ስቲፌን የተባለ የካሜሩን ተወላጅ፣ በሰኔ ወር ወደ ጣልያን አገር ለመሄድ ሲሞክር የደንብ ልብስ በለበሱ የጠረፍ ጠባቂዎች መደብደቡና መሰረቁ ለኢንዲፔንደንት ጋዜጣ ነግሮአል፡፡

“ሲደበድቡን ገንዘብ፣ ዶላሮች፣ ቴሌፎኖች ይጠይቁናል፣ ያለን ሁሉ ወሰዱት” ብሎ ስቲፌን ሊሚድያ ተናግሮአል፡፡ በመቀጠልም “እነሱ እንደሚሉት እኛ ገንዘብ ከሰጠናቸው፣ እነሱ እራሳቸው ወደ ጣልያን አገር እንደሚወስዷቸው” ብሏል፡፡
በተጨማሪም ስቲፌን ንግግሩ ሲቀጥል እሱና ሌሎች ተጓዦች በመጥፎነቷ የታወቀችውና በሊብያ የኮንትሮባንድ እምብርት የሆነችው ሳብራታ አጠገብ ወደ እምትገኘው እስር ቤት መተላለፋቸውና እዛም ባለሥልጣኖቹ እያንዳንዱ እስረኛ 155 ዩሮ ከከፈለ ነፃ እንደሚለቀቅ እስኪነግሩን ድረስ ለሦስት ሳምንት መቆየታቸውና በዛው በካሜሩን ተወላጅ ነጋዴ መከፈሉን ነው የተናገረው፡፡

በእንግሊዝ አገር የስደተኞችና ጥገኞች መብት ዳይሬክተር፣ ስቲቭ ቫልዴዝ ሲሞንድስ ስደተኞች ከጠረፍ ጠባቂዎች ወደ እስር ቤት ማእከላት እንደሚተላፉና እዛም ለነጋዴዎችና ለሌሎች እንደሚሸጡ ተናግሮአል፡፡
ሚስተር ቫልዴዝ ሲሞንድስ ይህ ምስቅልቅል የመጣው በሊቢያ የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ለሥልጣን መባለግ በር ስለከፈተ ነው ሲል ለኢንዲፔንደንት ጋዜጣ ነግሮአል፡፡

“ኃላፊነት ቢጤ ያላቸው የሚመስሉ ምናልባት ጭራሽ መደበኛ ክፍያ የማይከፈላቸው ወይም ተገቢ ክትትል የማይደረግባቸው እንደ ጠረፍ ጠባቂዎች” እንዳሉ ሚስተር ቫልዴዝ ሲሞንድስ አስጠነቅቋል፡፡ “በራሳቸው ተነሳሽነት ይሁን ወይም በሚሰጣቸው አመራር መሠረት ይሁን፣ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ ሥራ የተለመደ ነው”፡፡
በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መሠረት በሊቢያ ከሰባት መቶ ሺ እስከ አንድ ሚልዮን ስደተኞች በሊቢያ አሉ፣ በተጨማሪም ከ5ሺ እስከ 6ሺ በእስር ቤት ያሉት፡፡