ጣሊያን ውስጥ ያሉ ስደተኞች ጥበቃ ያንሳቸዋል
ሴንትሮ አስታሊ የተባለ, ለስደተኞች ድጋፍ የሚሰጥ የጄሱት ማእከል, ጣሊያን ውስጥ ያሉ ስደተኞች የሚያሳልፉትን ችግር የሚተነትን አዲስ ሪፖርት አሳተመ፡፡
ሪፖርቱ እንደሚገልፀው አውሮፓ ውስጥ ጥበቃ ለማግኘት የሚመጡ ህዝቦች ቁጥር መቀነስ ቢኖርም ሜድትራንያንን መሻገር የቻሉት ግን የጥበቃ ጥያቂያቸውን በሂደት ለማሳለፍና ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀል ከፍተኛ ችግሮች እያጋጠማቸው ነው፡፡
ጥናቱ በተጨማሪ እንደሚያሳየው ቢያንስ 10ሺ ስደተኞች ከአቀባበል ሲስተም ውጪ የተደረጉ ሲሆን መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶች በመላው ብሔራዊ ግዛት የተገደበ ወይም ምንም አይነት የማግኘት ሁኔታ የሌላቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡
ጣሊያን መጀመሪያ መቀበያ ማእከሎች ላይ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ቤት በመስጠት የምትተማመን ቢሆንም ትልልቅ አውታሮች ከከተማ ማእከላት የተነጠሉ፣ ከውጪው አለም ደካማ ዝቅተኛ ወይም አስቸጋሪ ግንኙነት አላቸው፡፡ መጨናነቅ እና ማንነትን ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ ውስጥም ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ መቀበያ ማእከሎች በተለይም ከሮም የሚለቁት ምንም አይነት ህጋዊም ሆነ ቁሳዊ ድጋፍ እንደማያገኙ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡
በዚህ አመት የካቲት ወር በ ዶክተርሰ ዊዛውት ቦርደርስ /ኤምኤስኤፍ/ የወጣው ሪፖርት እንደገለዸው በ2008 እና 2009 መካከል ጣሊያን ውስጥ ቢያንስ 10ሺህ የሚሆኑ ጥገኝት ጠያቂዎች እና ስደተኞች በሀገሪቱ የሰሜን ወሰን በ47 መደበኛ ያልሆኑ መጠለያዎች ያለመሰረታዊ ፍላጎቶች እና ህክምና የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከ5 አመት በታች የሆኑ ትናንሽ ልጆች በ17ቱ መጠለያዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ በኤምኤስፍ ሪፖርት መሰረት “መደበኛ ያልሆኑ ሰፍራዎች” ተብለው ከተፈረጁት ውስት – የተተው ወይም የተያዙ ህንፃዎች፣ የክፍት አየር መኖሪያዎች፣ ድንኳኖች፣ የጎጆ ቤቶች፣ ካቢኖች እና ኮንቴነሮችን ሲያካትት በተለይ በላዚዮ ክልል በመቀጠልም በፑግሊያ፣ ሲሲሊ፣ ካላባሪያ እና ፔዲሞንት ውስት እንደሚገኙ ይገልጻል፡፡
አይኦኤም የተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ኤጀንሲ በዚህ ዓመት ሪፖርት እንዳደረገው 119,310 ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በባህር ወደ ጣሊያን እንደ መደበኛ ያልሆነ ስደተኛ በመሆን የገቡ ሲሆን በ4 አመታት ውስጥ ባጠቃላይ ዝቅተኛ መጠን ነው፡፡
ሆኖም ከዩኤንኤችሲአር (የተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ኤጀንሲ) የቅርብ ጊዜ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚመጡ ስደተኞች በ74 በመቶ በ2010 የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ቢቀንስም በጉዞ ላይ ህይወታቸው የሚያጡ ስደተኞት ብዛት ከእጥፍ በላይ ሆኗል፡፡
ሳሚፎ (ጣሊያን ውስጥ የስደተኞችን ጥበቃ እና ጤና የሚያበለፅግ ማእከል) ሪፖርት እንዳደረገው በተለይ ከሊቢያ ማቆያ ማእከል የሚመጡት ላይ የሚደርስባቸው ጥቃት እየጨመረ ነው፡፡ የህክምና እና የአእምሮ ምርመራዎች በአብዛኛው እንደሚያሳዩት ስደተኞች አእምሮን የሚያጨናንቅ ልምድ ያዳብራሉ፡፡ የማማከር ማእከሎቹን ከሚጎበኙ ስደተኞች ውስት 1/4ኛው ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እና ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡
በ10/9/2009 በሚላን, ጣሊያን አካል ጉዳተኛው ስደተኛ መንገድ ላይ ገንዘብ ሲለምን፡፡
TMP – 16/05/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ