ሞሮኮ በ2018 ወደ አውሮፓ በመሄድ ላይ የነበሩ 89,000 ስደተኞች አስቀርታለች

የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ጃንዋሪ 17/2019  ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው ሀገሪቱ 89 ሺ ህገ ወጥ ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ከመሄድ አስቀርታለች።  ይህ ቁጥር ወደ አውሮፓ ለመሄድ አስበው ከሚያዙ ስደተኞች ቁጥር 37 በመቶ ናቸው። ሞሮኮ በሰሜን አፍሪካ ካሉ የስደተኞች መውጫ በሮች ዋነኛዋ ናት።  

በ2018 ብቻ በሞሮኮ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሄድ ከተያዙት ህገወጥ ስደተኞች  80%ቱ ሞሮካውያን አይደሉም። እነዚህ ስደተኞች በሞሮኮ በኩል ወደ ስፔን ለመድረስ የባህር እና የምድር አማራጮች ወስደው ለመውጣት ያሰቡ ናቸው።   ወደ 30 ሺ የሚጠጉ በባህር ላይ እያሉ ከሞት የዳኑ ሲሆን ከ5,600 በላይ ደግሞ በፈቃደቸው ወደየሀገራቸው እንዲመለሱ ዕድል ተሰጥተዋቸዋል።  የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በመግለጫው በ 2018 ብቻ  229 ህገወጥ ስደት የሚመሩ ኔትወርኮች ተበጣጥሰዋል።

 ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ በሚደረግ ጉዞ በሊብያ በኩል ወደ ጣልያን የነበረውን መንገድ፡ ጣልያን በህገ ወጥ ስደተኞች እና ህገወጥ ደላሎች ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝዋ ምክንያት ሞሮኮ ብዙ ስደተኛ የሚወጣባት በር ሆናለች። ሞሮኮ ለአፍሪካውያን ስደተኞች ቪዛቸውን እየነጠቀች ባህር እንዳያቋርቱ ታደርጋለች። ይሁንና ብዙ ስደተኞች በመሬት አቋርጠው ለመውጣት ይሞክራሉ። ለሎች ደግሞ ለህገ ወጥ ደላሎች ክፍያ በመፈጸም 14 ኪሎሜትር ርቀት ያለውን የባህር ጉዞ ይመርጣሉ።  በጣም አጭር መንገድ ይሁን እንጂ በ2018 ሪኮርድ ከተደረገ አጠቃላይ 2217 የሟቾች ቁጥር 744ቱ በዚህችው የሜዲትራንያን ክፍል ላይ ያጋጠመ ሞት ነው።  

ይሄንን የህገ ወጥ ስደት ለመከላከልና ህገ ወጥ ደላሎችን ለማጥፋት ይረዳ ዘንድ ኦክተበር 2018 ላይ የአውሮፓ ህብረት 140 ሚልዮን ዩሮ ለሞሮኮ ድጋፍ ሰጥተዋል። ከዚሁ ድጋፍ 30 ሚልዮኑ ገቢ ተደርገዋል።  

በአሁኑ ሰዓት የሞሮኮ ፖሊስ ህገወጥ ስደተኞች ይገኝባቸዋል ተብለው በሚጠረጠሩ አከባቢዎች ዕለታዊ ዳሰሳ እና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።  እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ በሽዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሞሮኮ ላይ እየታገቱ ወደ ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ይወሰዳሉ።  ከተያዙ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲወስኑ ሞሮኮ ፈጣን ምላሽ እየሰጠች መሆናም ተገልጸዋል።  

በሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር የስደት እና ድንብር ጉዳዮች ዳይሬክተር ካህሊድ ዞሮሊ ለሮይተርስ   ወረቀት የሌላቸው ከሰሃራ በታች ካሉት ሀገራት የመጡ ህገ ወጥ ስደተኞች ሲገኙ ከደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አውጥተን ወደ ሌሎች ከተሞች እንልካቸዋለን።” ብለዋል።  በዱባዊ የሀገሪቱ ክፍል ከመቆየት ወደ እነ ማራከች የመሳሰሉ ከተሞች ቢዘዋወሩ ይሻላቸዋል።”  

በ2018 ወደ አውሮፓ ከሄዱ ህገ ወጥ ስደተኞች የላቀ ቁጥር የያዘች አውሮፓዊት ሀገር ስፔን ሆናለች።  እንደ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገለጻ  በ2018 ብቻ ከ57 ሺ በላይ ህገ ወጥ ስደተኞች ሜዲትራንያን ባህር አቋርጠው አውሮፓ ደርሰዋል።  

TMP – 27/01/2019  

የፎቶ ካፕሽን፡ በስፔንዋ መሊላ እና በሞሮኮ መካከል የታጠረ አደገኛ አጥር  

ፎቶ ክሬዲት: ሻተርስቶክ