የኣለም ባንክ ወደ ኤውሮጳ ሚያመሩ ኣፍሪካውያን ስደተኞች ለምቀነስ የሚያግዝ የ100 ሚልዮን ዶላር ኣሚሪካ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ሰጠ።

የዓለም ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የሕገ ወጥ አፍሪካውያን ስደት ለመግታት ትኩረት አድርጎ ለሚሰራበት ፕሮግራም የሚውል የ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደተሰጠ ከዚያች ሀገር በተሰራጨው ዘገባ ተገልጻል፡፡

ይህ በ2017 የመጀመሪያዎቹ ወራቶች ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው መርሃ ግብር በአምስት የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ካምፓች ሰፍረው ለሚገኙ ስደተኞች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወታቸው በማሻሻል በቀጣይ ለከፋና የተራዘመ የስደት ኑሮ እንዳይዳረጉ ያለመ እንደሆነ ተገልጻዋል፡፡

መርሃግብሩ በትግራይ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ዓፋርና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የስደተኞች ጣቢያ ዋና ትኩረቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ከስደተኞች ባሻገር የአካባቢውን ነዋሪዎች ጨምሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ይህ በአይነቱ ትልቁና ጥቅሙም ከፍተኛ እንደሆነ የታመነበት መርሃ ግብር መጀመር አስመልክቶ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር ዶ/ር ምስራቅ መኮንን መርሃ ግብሩ የስደተኞችንና የአካባቢው ማህበረሰብ የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ለውጥና ጥቅም እንደሚመዘገብበት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በበለጠ የኤርትራ፣ የደቡብ ሱዳን፣ ሪፖብሊክና ሶማልያ 800,000 ስደተኞች ተቀብላ የምታስተናግድ ሀገር በመሆንዋ ይህ በዓለም ባንክ ልዩ ትኩረት አግኝቶ ከፍተኛ ገንዘብ የተበጀተለት መርሃ ግብር – ሀገሪቷን እንደመሸጋገሪያ ተጠቅመው በሰሜን አፍሪካና ማዕከላዊውን የባህር ክልል አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ ህገ ወጥ ስደተኞችን ከሀገራቸው ሳይርቁ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው እንዲያሻሽሉ የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ተጠልለው ከሚገኙ 800,000 ስደተኞች መካከል 120,000 ስደተኞች ኤርትራውያን መሆናቸው ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡