ግሪክ በአውሮፓና ቱርክ መካከል የሚደረገው ውል እንደምትደግፍ እንደገና አረጋገጠች
ፎቶ፡ Ekathimerini.com. ያኒስ ሙዛላሰ፣ የግሪክ ስደተኞች ፖሊሲ ሚኒሰቴር
የግሪክ ስደተኞች ሚኒስቴር ያኒስ ሙዛላሰ፣ አገራቸው ወደ አገሯ በኤጂያን ባሕር በኩል የሚገቡት ሕገ ወጥ አዲስ ስደተኞችን ወደ ቱርክ መልሳ እንድትልካቸው የሚደግፍ በአውሮፓና ቱርክ የተደረገው ውል እንደምትደግፍ እንደገና አረጋገጡ፡፡
ካቲሜሪኒ ሙዛላስ ከአገር ውስጥ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፣ “ምንም እንኳ [በቱርክና አውሮፓ መካከል የተደረገው ስምምነት ችግር ቢኖረውም] ስምምነቱ ለግሪክ ጠቃሚ መሆኑን አውሮፓ ማብራራት አለባት” ብለዋል፡፡
ሙዛላስ ንግግራቸው በመቀጠል የስደተኞችና የስደተኛ ጥገኞች ወደ አውሮፓ በብዛት እንዲገቡ በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች መሪነት በገንዘብ እየተረዱ መሆናቸው ቢታወቅም፣ ሊገታ የሚቻለው ከአውሮፓና ቱርክ ጋር ስምምነት በማድረግ ነው፡፡
“የዚሁ የስደተኞችና የስደተኛ ጥገኞች ፍልሰት መጠን ሊፈታ የሚቻለው የዚሁ ዓይነት ስምምነቶች በማድረግ ብቻ ነው” ብለዋል ሙዛላስ፡፡
በአገሩ የስደተኞች ሚኒስቴር ሪፖርት መሠረት ወደ ግሪክ የሚሻገሩት ሕገ ወጥ ስደተኞች ቍጥር በአውሮፓና ቱርክ መካከል የተደረገው ስምምነት በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ በጎላ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
በቅርቡ የወጣው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አኃዝም የሚያሳየው የደራሾች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ነው፡፡ በዚሁ ዓመት የመጀመርያ 10 ወሮች 23,000 ሰዎች ከቱርክ ወደ ግሪክ ተሸግረዋል፡፡ ይኸውም ሲነፃፀር ባለፈው ዓመት በግምት 170,000 ሰዎች በ2015 እ.አ.አ 780000 ሰዎች ድንበር ተሻግረው ገብተዋል፡፡
ከ2015 እ.አ.አ ጀምሮ አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ስደተኞችን ላለማስገባትና ወደ አውሮፓ ኅብረት ለመግባት ለስደተኞች እጅግ አስቸጋሪና አደገኛ እንዲሆን ጠረፎቻቸው በአጥር መዝጋት ጀምረዋል፡፡ በማሰዶኒያ/መቅዶኒያና ግሪክ፣ በሃንጋሪና በሰርቢያ እንደዚሁም በአውስትሪያና በጣልያን መካከል ባሉት ድንበሮች የኤሌክትሪክ አጥርና ግነቦች ተተክለዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ