እንግሊዝ በኤስያና ላቲን አሜሪካ ስደተኞችን ለማቋቋም የሚያግዝ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ለገሰች

የተባበሩት መንግስታት የሰደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ለኤስያና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ስደተኞችን ደግሞ ለማቋቋም

ለሚያካሂደው ተግባር ነው 30 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ከእንግሊዝ መንግሰት ያገኘው፡፡

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሬza ሜይ ይህ የመልሶ ማቋቋምያና ሰብአዊ ድጋፍ ስደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች

ለሰብአዊ ጥቃትና ችግር እንዳይጋለጡ ለመከላከል የሚያግዝ እንደሆነ በጣልያኗ ማልታ በፌብርዋሪ 3/2017

በተደረገው የአውሮፓ ህብረት ሰብሰባ ገልጸዋል፡፡ ይህም ስደተኞች በአደገኛው አስፈሪ ጉዞ ወደ አውሮፓ የሚያደርጉት ስደት

በመከላከል ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ኤስያና ላቲን አሜሪካ ተመልሰው እንዲቋቋሙ የሚያግዝ ከመሆኑም ባሻገር

የበለጸጉ አገራት ለአዳዲሶቹ የላቲንና ኤስያ አገራት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የአውሮፓ ሀገሮች በህገወጥ ስደተኞች

ምክንያት እያጋጠማቸው ያለውን ጫና ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡ የሃገሮቹ ስም እስካሁን ያልተረጋገጠ ሲሆን

ስደተኞን ለማስፈረና ለማቋቋም የተሻሉ እንደሚሆኑ ግን ተገልጿል፡፡ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት 30000 ህገወጥ

ስደተኞችን ለመመለስም ታቅዷል፡፡

ከተሳታፊ ሃገራት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በኤስያና ላቲን አሜሪካ አገራት የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከሚሽንና በአለምአየፋ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር የሚካሄድ

ነው፡፡ ተሬሳ ሜይ ይህ የ3ዐ ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ስደተኞች በጣም አደገኛ በሆነ ሁኔታ ወደ አውሮፔ የሚያደርጉት ጉዞ

ለማስቀረትና ወደ አገራቸው ተመልሰው ተረጋግተው እንዲኖር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

እንግሊዝ በተጨማሪ ሴቶች በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በሚያደርጉት ጉዞ የሚያጋጥማቸውን ጠቃት

ለመከላከል የሚያስችል ልዩ ፈንድ ያዘጋጀች ሲሆን ከዚህ ውስጥም በግሪክና ምስራቅ አውሮፓ በተከሰተው እርጥበት

አዘልና ውርጭ የአየር ሁኔታ ለአደጋ የተጋለጡ ህገወጥ ስደተኞች ህይወታቸውን ለመታደግና ለህክምና የሚውል ነው፡፡

ገንዘቡ በተጨማሪ የተለያዩ ቤተሰቦችን ለማገናኘትና በበጎ ፍቃደኝነት ለሚመለሱ ስደተኞችን ለማሰባሰብ በሱዳን

ለሚቋቋመው አዲስ የመጠለያ ጣብያ ይውላል ተብሏል፡፡

ይህ እንግሊዝ ከ2015 ጀምሮ ለሰብአዊ ድጋፍ ያደረገችው የገንዘብ መጠን ወደ 1ዐዐ ማልዮን ፓውንድ ከፍ

የሚያደርግ ነው፡፡

የእንግሊዝ አለምአጠፍ ልማት ሚኒስተር ኘሪቲ ፓተል ይህ የገንዘብ ድጋፍ እንግሊዝ በጣም ለአደገኛ ህይወት

የተጋለጡ ስደተት ድጋ÷ን እንደሚፈልጉ ያሳየችበት እንደሆነና ይህም በገዛ ፍቃዳቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ

ሀገራዠው ለሚመለሱ ጎልማሶች ፣ ሴቶችና ህጻናት የገጠማዠው አስቸጋሪ ሁኔታ የሚገታና በቀጣይ

ህልውናቸውን እነዲያረጋግጡ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ይህ በእነዲህ እንዳለ እንግሊዝ በሊብያ ውስጥ ያለው ሰብአዋ ቀውስ ለመከላከል 2 ማልዮን ፓውንድ

እንዲሁም የሊቢያ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎችን በማጠናከር ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን ደላሎችና የጦር መሳሪያን

ለመከላከል 517ሺ ፓውንድ ድጋፍ እንደምትሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቃል ገብተዋል፡፡