ስዊዘርላንድ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን የሚጎዳ አዲስ ህግ ተግባራዊ ልታደርግ ነው
በቅድስት ጋለን የተሰየመው የስዊዘርላንድ ችሎት ከኤርትራ የሚመጡ ህገወጥ ስደተኞች የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ
ውድቅ የሚያደርግ ሕግ ኣፀደቀ።
ኣዲሱ ሕግ ከጥር 2፡ 2017 ጀምሮ የጸደቀው ህግ ቀደም ሲል ጥገኝነት የሚጠየቁ ኤርትራውያን አስመልክቶ የነበረው ህግ
“አሳማኝ” ወይም ፍትሃዊ አይደለም ብሏል፡፡
ስዊዘረላንድ በህገወጥ መንገድ ከአገራቸው የመወጡ ህገወጥ ስደተኞች የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጠያቄ በዚህ
እያስተናገደች መቀጠል እንደሌለባትም ይደነግጋል፡፡
በስዊዘርላንድ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ ኤርትራውያንን ጉዳይ ሲመረምር መቆየቱና እነዚህ ስደተኞች ተመልሰው ወደ
ሀገራቸው እንደሚገቡና ከገቡ በኋላም ምን አይነት ጫናና ኢሰብአዊ አያያዝ እንደማይደረግባቸው ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ የሌለውና ስዊዘርላንድ ለኤርትራዊያን ስደተት በሯን እንድትዘጋ የሚያደርግ ነው፡፡
በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሰደዱ ኤርተራውያን በቁጥር ከፍተኛውን ደረጃ ከያዙት መካከል ሲሆኑ
በአሁኑ ሰዓት 25000 ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ጥገኝነት እንደጠየቁና ይህም በ2016 ከነበረው
በ15000 ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ