የበርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች ሬሳ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ተገኛ

TMP – 28/02/2017

የሊቢያ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች የሰባ አራት አፍረካዊያን ስደተኞች ሬሳ በስሜናዊው    የሀገሪቱ የባህር ዳርቻ ዛውያ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለፀ፡፡

በጥር 21 ከተገኙት ሬሳዎች አብዛኛዎቹ  ከሳሃራ በታች የመጡ ጎልማሶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥም ሦስቱ ሴቶች ናቸው፡፡

የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ማህበር እንደገለፀው አባላቱ ሬሳዎቹን  ከባህር ለመሰብሰብ 6 ሰዓታት የፈጀባቸው ሲሆን አሁንም ያልተገኙ ሬሳዎች ይኖራሉ የሚል ስጋት እንዳለው አስታውቋል፡፡

የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ማህበር ቃለ አቀባይ መሐመድ አልማስራቲ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደገለፁት ከሆነ 120 ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረችው ከፕላስቲክ የተሰራች ጀልባ ስብርባሪዋ በመገኘቱ ተጨማሪ ያልተገኘ ሬሳ የመኖሩ እድል የሰፋ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ገለፃ ከሆነ ጀልባዋ ከቀናት በፊት ከሊቢያ ወደ ጣልያን ስድተኞችን ጭና የተነሳች ሲሆን ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ በጉዞ ላይ እያለች ሞተርዋን በማላቀቃቸው ለቀናት ስትንሳፈፍ ቆይታለች፡፡

ይህ አዲስ ክስተት ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በስደተኞች ላይ ያላቸው አያያዝ እየከፋ መምጣቱን ያሳያል ሲሉም የረድኤት ድርጅቶች ስጋታቸው ገልፀዋል፡፡ይህ ክስተት አስደንጋጭ  ያሚያደርገው ብዛት ያላቸው ስድተኞች በአንድ ጉዞ መሞታቸው ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ በስድተኞች ላይ የተፈፀመ የጭካኔ ቅጣት በመሆኑ ነው” ብለዋል IOM ቃለ አቀባይ፡፡

የአውሮፓ የድንበርና ባህር ዳርቻ ጥበቃ ድርጅት እንደገለፀው ከሊቢያ ወደ ጣልያን ባለው የባህር መተላለፍያ መሰመር ባለፈው አመት 4,579 ሰዎች በመሞታቸው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በጥር 2017 ብቻ ግን 240 ስደተኞች መሞታቸው ተዘግቧል፡፡ ይህም ሁሉም በባህር ላይ ሰጥሞው ያልወጡ ስደተኞች ሙሉ  መረጃ ስላልተጠናቀረ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ባለፈው ወር የአውሮፓ ህብረት በሊቢያና በጣልያን የስደተኞች ህገ ወጥ ጉዞን ለመግታት፣የሊቢያ የባህር ክልል ጠባቄዎች ለማሰልጠንና በሊቢያ የስደተኞች መጠለያ ለማቋቋም የተደረሰው ስምምነት በገንዘብ ለመደገፍ መወሰኑ ይታወቃል፡፡