ከግማሹ በላይ አዉሮፓዉያን ሙስሊም ስደተኞችን አለመቀበል ይደግፋሉ

TMP – 20/02/2017

መሰረቱ በለንደን የሆነዉ በዓለም አቀፍ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር የሚሰራ ቻታም ሃዉስ የተባለ ተቋም ባካሄደዉ ጥናት ከግማሽ በላይ አዉሮፓዉያን የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ህዝብ ከሚበዛባቸዉ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞችን ይቃወማሉ፡፡

ተቋሙ በ10 የአዉሮፓ ሃገራት 10 ሺህ ሰዎች ጠይቆ ባገኘዉ መልስ ከእነዚህ 55% የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ከሚበዛባቸዉ የመካከለኛዉ ምስራቅና የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የሚመጡ ሙስሊም ስደተኞች እንዳይገቡ ይቃወማሉ፡፡ ተቋሙ “ከእስልምና ተከታይ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞች መቆም አለበት፡” በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ አይስማሙም የሚል ጥያቄ ካቀረበላቸዉ መካከል 20% አንስማማም፡ 25% ደግሞ በዚህ ጉዳይ ምን እንደሚወስኑ እንደማያዉቁ የገለጹ ሲሆን በአጠቃላይ በጉዳዩ እንደማይስማሙ የገለጹት ከ32% ያልበለጡ ናቸዉ፡፡

ከ10 የተጠኑት የአዉሮፓ ሃገራት በስምንቱ ሃገራት የሚገኙ አብዛኛዎቹ ከእስልምና ተከታይ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞች እንዲከለከሉ ተስማምተዋል፡፡ ከነዚህ በፓላንድ 71%፣ በስፔን 41% ስምምነታቸዉ ገልጸዋል፡፡

“የጥናታችን ዉጤት ዉስብስብና ጸብ አጫሪ ነዉ፡” ያሉት ተንታኞቹ ይህ ከሙስሊም ሃገራት የሚመጡ ስደተኞች እንዲከለከል የሚገልጽ የህዝብ ተቃዉሞ በትራምፕ ኣሜሪካ ብቻ የሚታይ እንዳልሆነና በትክክልም አመለካከቱ እየተስፋፋ እንደ ሆነ ያሳያል፡” ብለዋል፡፡

ሙስሊም ስደተኞች እንዳይገቡ ከሚደግፉት በእድሜ የገፉ በተለይ ከስራ በጡረታ የተገለሉ፤ ለሙስሊም ስድተኞች ተቃውሞቸው በጣም ከፍተኛ ጥልቀት የነበረው ሲሆን ከ30 አመት በታች ያሉ ግና ለሙስሊም ስደተኞች ተቃውማቸው አነስተኛ ነው፡፡ በትምህርት ደረጃቸው ስንመለከታቸው 59% የሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ብቻ ያጠናቀቁ ለሙስሊም ስደተኞች የሚቃወሙ ሲሆን ፤ የመጀመርያ ድግሪ ካላቸው በግማሽ የሚያንሱ ብቻ በስፋት ለሙስሊም ስደተኞች አገራቸው እንዳይገቡ ይቃወማሉ፡፡

በመንግስታቸዉ ፖሊሲ እንደተገለሉ አድርገዉ በሚያስቡ መራጮች፣ ተቀዋሚዎች የበላይነት እንደሚኖራቸዉ የገለጸዉ ጥናቱ ሙስሊም ስደተኞችን ከተቃወሙት 2/3 የሚሆኑት በኑሮአቸዉና ህይወታቸዉ ደስተኛ ያልሆኑ ናቸዉ ብሏል፡፡ ሙስሊም ስደተኞችን ከተቃወሙት ¾ የሚሆኑት ግራ ዘመም ፖለቲካ የሚያራምዱ ሲሆን ቀኝ ዘመም ፖለቲካ ከሚያራምዱት መካከል 1/3 የሚሆኑት ሙስሊም ስደተኞችን ይቃወማል፡፡